የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g94 1/8 ገጽ 27-28
  • ደስታን አለገንዘብ መግዛት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ደስታን አለገንዘብ መግዛት
  • ንቁ!—1994
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አለገንዘብ መግዛት
  • ለደስታ የሚከፈለው ዋጋ
  • በአሁኑ ጊዜ ገንዘብን በጥበብ መጠቀም
  • በአሁኑ ጊዜም ቢሆን ደስታ ሊገኝ ችሏል
  • ለገንዘብ ሚዛናዊ አመለካከት ይኑርህ
    ንቁ!—2015
  • ከገንዘብህ ወይ ከሕይወትህ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
  • የገንዘብ አያያዝ
    ደስተኛ ቤተሰብ ሊኖርህ ይችላል
  • ገንዘብ
    ንቁ!—2014
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—1994
g94 1/8 ገጽ 27-28

ደስታን አለገንዘብ መግዛት

በቆላማ አካባቢ ረዘም ያለ ጉዞ በእግርህ ከተጓዝህ በኋላ በውሃ ጥም ተቃጥለህ አንድ መንደር ትደርሳለህ። ወዲያው ቀዝቃዛ መጠጥ ይገኛል የሚል ማስታወቂያ ትመለከትና ትደሰታለህ። ግን መጠጡን የምትገዛበት ገንዘብ እንደሌለህ ትገነዘባለህ።

ባለሱቁ ሁኔታህን ተመልክቶ ‘አይዞህ ግባ፣ መጠጡን ውሰድና ጠጣ፣ ምንም ገንዘብ አያስፈልግህም’ ይልሃል። ወዲያው እንዲህ ላለው ልግስና ከልብህ ማመስገንህ አይቀርም። ይሁን እንጂ ‘እንዴት እንዲህ ሊሆን ይችላል? እንዴት አለገንዘብ መግዛት እችላለሁ?’ ብለህ ትጠይቃ⁠ለህ።

አለገንዘብ መግዛት

ይህ የገለጽነው ሁኔታ የማይሆን ነገር መስሎ ቢታይም በገጽ 21 ላይ የተጠቀሱት ካረልና ጁልያን እንዲህ ያለ ሁኔታ አጋጥሟቸዋል። ገንዘብ ደስታ የሚያስገኝላቸው መስሏቸው ነበር። ይሁን እንጂ ካረል እንዲህ ብላለች:- “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ስለ ገንዘብ የነበረኝን አመለካከት ለወጠው። ገንዘብ ሊገዛ ከሚችለው ከማንኛውም ነገር የሚበልጠውን በምድራዊ ገነት ለዘላለም የመኖር ተስፋ እንዳገኝ አስቻለኝ።” ሚልየነር ለመሆን ይጣጣር የነበረው ጁልያን ደግሞ “እውነትን ከመጽሐፍ ቅዱስ ባወቅኩበት ጊዜ ሚልየነር ወደ መሆን ግቤ ለመድረስ ተቃርቤ ነበር” ይላል። ኪዮሺ ቶሞሚትሱ የተባለው ጃፓናዊ የገበያ አዳራሽ ባለቤትም በተመሳሳይ ከማንኛውም ነገር ይበልጥ ለሥራው ቅድሚያ ይሰጥ ነበር። ቤተሰቡን መንከባከብ ሁለተኛ ደረጃ የተሰጠው ጉዳይ ነበር። “ለቤተሰቤ የወደፊት ሕይወት የሚያስፈልጋቸውን ገንዘብ በማከማቸት የማስደስታቸው ይመስለኝ ነበር” ይላል። ኪዮሺ ስለ ገንዘብና ስለ ቁሳዊ ንብረት የነበረውን አመለካከት እንዲለውጥ ያስቻለው ምን እንደሆነ ተጠይቆ ሲመልስ “በምሳሌ 23:​23 ላይ ‘እውነትን ግዛት አትሽጣትም’ እንደሚሉት ያሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ናቸው” ብሏል።

‘ግን እውነትን መግዛት የምችለው እንዴት ነው?’ ብለህ ትጠይቅ ይሆናል።

ለደስታ የሚከፈለው ዋጋ

ጊዜ መመደብ ይጠይቅብሃል። ክርስቲያኑ ሐዋርያው ጳውሎስ “ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ጊዜውን ዋጁ” ብሏል። (ኤፌሶን 5:​15–17) በአካባቢህ የሚኖሩ የይሖዋ ምሥክሮች አንተን በሚመችህ ጊዜ አለምንም የገንዘብ ክፍያ ስለ አምላክ ቃል እውነት ቢያነጋግሩህ ደስ ይላቸዋል።

እንደዚህ ባለው ውይይት ለመካፈል ታመነታለህን? የምታመነታ ከሆነ ኢየሱስ የተናገረው ቃል ሊያበረታታህ ይገባል:- “ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ደስተኞች ናቸው፣ ይጠግባሉና።” ኢየሱስ አድማጮቹ ደስታ ሊያገኙ የሚችሉበትን መንገድ ሲጠቁም “ስለሚያስፈልጋቸው መንፈሳዊ ነገር የሚያስቡ ደስተኞች ናቸው፣ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና” ብሏል። (ማቴዎስ 5:​3, 6 አዓት) ወደ ደስታ የሚያስገባህን የይለፍ ወረቀት ሊሰጥህ የሚችለው ብቸኛ ባለ ሥልጣን ይህ የሰማይ መንግሥት ወይም የአምላክ መንግሥት ነው።

ታዲያ ገንዘብ በሕይወትህ ውስጥ ምን ሚና ሊኖረው ይገባል? መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ጉዳይ ተግባራዊ የሆነ መመሪያ ይሰጣል።

በአሁኑ ጊዜ ገንዘብን በጥበብ መጠቀም

የአምላክ ቃል “እግዚአብሔርን ከሀብትህ አክብር” ይላል። (ምሳሌ 3:​9) በዚህ ምክንያት ከአምላክ እውነተኛ ደስታ ለማግኘት የሚፈልጉ ሁሉ ገንዘባቸውን አምላክን በሚያስደስት መንገድ ይጠቀሙበታል። ቤተሰባቸው የሚያስፈልገውን ቁሳዊ ነገር ለማቅረብ ይጥራሉ። (1 ጢሞቴዎስ 5:​8) በእምነት የሚዛመዷቸውን ሰዎች ይረዳሉ። በተጨማሪም በመጽሐፍ ቅዱሶችና ይህን መጽሔት በመሰሉት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች አማካኝነት የሚከናወነውን መንፈሳዊ ትምህርት የማሠራጨት ሥራ በፈቃደኝነት በሚሰጡት መዋጮ ይደግፋሉ።

የአምላክ መንግሥት ፍቅረ ንዋይንና ራስ ወዳድነትን ከሰብዓዊ ማኅበረሰብ ውስጥ ጠራርጎ እንደሚያጠፋ ስለሚያውቁ ለጥፋት በተመደቡ እቅዶች ላይ ገንዘባቸውን በማፍሰስ ተዘናግተው ከመንገዳቸው እንዳይወጡ ይጠነቀቃሉ። (ዳንኤል 2:​44) “ምግብና ልብስ” ካገኙ ለሕይወት አስፈላጊ ለሆኑት ነገሮች ብቻ ቅድሚያ በሚሰጥ አኗኗር ይረካሉ።​—1 ጢሞቴዎስ 6:​8

በአሁኑ ጊዜም ቢሆን ደስታ ሊገኝ ችሏል

ሱ የተባለች እንግሊዛዊት እንዲህ በማለት ትተርካለች:- “ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር ስገናኝ ካስተዋልኳቸው የመጀመሪያ ነገሮች አንዱ እነዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች የሚመላለሱና ሙሉ በሙሉ በአምልኮታቸው የተመሰጡ ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን ነገር ሁሉ ያገኙ ሆነው መታየታቸው ነው።” ባልዋም ጆን ተመሳሳይ ነገር አስተውሏል። እንዲህ በማለት ይገልጻል:-

“አብዛኞቹ ሰዎች የሚኖሩበትን ሁኔታ ልረዳ የቻልኩት የመጽሐፍ ቅዱስን እውቀት ካወቅኩ በኋላ ነው። የሚደክሙበት ነገር ሁሉ በገንዘብ ላይ የተመካ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ደስታ በዚህ መንገድ ሊገኝ እንደማይችል እንዳውቅ ረድቶኛል። አሁን ደስታ ራሱን የቻለ ግብ ሳይሆን ለሌሎች በጎ ከማድረግ የሚገኝ ውጤት እንደሆነ ተገንዝቤአለሁ።”

ጆንና ሱ የአምላክን መንግሥትና ጽድቁን ካስቀደሙ የሚያስፈልጋቸው ቁሳዊ ነገር በሙሉ እንደሚጨመርላቸው ኢየሱስ የሰጠው ተስፋ እውነት መሆኑን ሊመሠክሩ ከቻሉት አምስት ሚልዮን የሚያክሉ የይሖዋ ምሥክሮች ሁለቱ ብቻ ናቸው።​—ማቴዎስ 6:​33

ጥም አርኪ የሆነውን የእውነት ውሃ በመፈለግ ላይ ነህን? ባለጠጋም ሆንክ ድሃ “እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ፣ ወደ ውኃ ኑ፣ ገንዘብም የሌላችሁ ኑና ግዙ ብሉም። ኑ ያለ ገንዘብ . . . ግዙ” ለሚለው የአምላክ ትንቢታዊ ጥሪ ምላሽ በመስጠት ደስታ ልታገኝ ትችላለህ። (ኢሳይያስ 55:​1) ይህ ጥሪ ዘመኑ ያለፈበት አይደለም። አሁኑኑ ጊዜው ሳያልፍ ተጠቀምበት።

[በገጽ 28 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ገንዘብ ቤተሰባችን የሚያስፈልገውን ቁሳዊ ነገር ለማቅረብና ሌሎችን ለመርዳት ከተመቀምንበት ደስታ ሊያስገኝልን ይችላል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ