የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘የሰው ሁለንተናዊ ግዴታ’
    መጠበቂያ ግንብ—1997 | የካቲት 15
    • 13. (ሀ) መክብብ 9:​4, 5 ታዋቂነትና ሥልጣን ለማግኘት ስለ መጣጣር ተገቢ አመለካከት እንድንይዝ የሚረዳን እንዴት ነው? (ለ) ሕይወት ይህ ብቻ ከሆነ የትኞቹን እውነታዎች መቀበል ይገባናል? (የግርጌ ማስታወሻውን ተመልከት።)

      13 እንዲህ ያለው ታዋቂነት ወይም ሥልጣን በመጨረሻ ምን ያስገኛል? አንዱ ትውልድ አልፎ ሌላው ሲተካ ታዋቂ ወይም ባለ ሥልጣን የነበሩት ሰዎች ከዓለም መድረክ ያልፋሉ፤ በኋላም ይረሳሉ። እንደ አብዛኞቹ ፖለቲከኞችና የጦር መሪዎች ሁሉ በአንድ ወቅት የሕንጻ ባለ ሙያዎች፣ ሙዚቀኞችና ሌሎች አርቲስቶች እንዲሁም የማኅበራዊ አንቅስቃሴ አራማጆች የነበሩት ሁሉ ሁኔታቸው ከዚህ የተለየ አይደለም። ከ17ኛው እስከ 18ኛው መቶ ዘመን ባሉት ዓመታት መካከል በእነዚህ ሙያዎች ካገለገሉት ግለሰቦች ምን ያህሎቹን ታስታውሳለህ? ሰሎሞን ይህን ጉዳይ እንዲህ በማለት መቋጨቱ ተገቢ ነው:- “ያልሞተ ውሻ ከሞተ አንበሳ ይሻላልና . . . ሕያዋን እንዲሞቱ ያውቃሉና፤ ሙታን ግን አንዳች አያውቁም፤ መታሰቢያቸውም ተረስቷልና።” (መክብብ 9:​4, 5) ሕይወት ይህ ብቻ ከሆነ በእርግጥም ታዋቂነት ለማትረፍ ወይም ሥልጣን ለመጨበጥ መሯሯጥ ከንቱ ነው።a

  • ‘የሰው ሁለንተናዊ ግዴታ’
    መጠበቂያ ግንብ—1997 | የካቲት 15
    • a በአንድ ወቅት መጠበቂያ ግንብ የሚከተለውን አስተዋይነት የተሞላበት አስተያየት ሰንዝሮ ነበር:- “ሕይወታችንን ከንቱ ነገሮችን በማሳደድ ልናሳልፈው አይገባም፤ . . . ሕይወት ይህ ብቻ ከሆነ ሁሉ ነገር ከንቱ ነው ማለት ነው። ይህ ሕይወት ወደ አየር ተወርውሮ ተመልሶ ትቢያ ላይ እንደሚወድቅ ኳስ ነው። ታይቶ እንደሚጠፋ ጥላ፣ እንደሚረግፍ አበባ፣ ሲቆረጥ ወዲያው ጥውልግ እንደሚል ቅጠል ነው። . . . የሕይወታችን ርዝማኔ በዘላለማዊነት ሚዛን ስትለካ ከቁጥርም የማትገባ ቅንጣት ነች። በዘመናት ጅረት ውስጥ እንደ አንድ ጠብታ እንኳን አትሆንም። በእርግጥም [ሰሎሞን] በሕይወት ውስጥ ያሉትን ብዙ ሰብዓዊ ፍላጎቶችና የሥራ እንቅስቃሴዎች ከገመገመ በኋላ ከንቱ ናቸው ማለቱ ትክክል ነው። ሕይወታችን በቅጽበት ያልፋል፤ መወለዳችን ምንም ፋይዳ ያለው አይመስልም፤ ወደፊትም ተወልደው ከሚሞቱት በቢልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች መካከል ጭራሽ በሕይወት እንደነበርን እንኳን የሚያውቁት እጅግ በጣም ጥቂት ናቸው። ይህ አፍራሽ አስተሳሰብ የተጠናወተው ወይም ተስፋ የቆረጠ ሰው አስተያየት አይደለም። ሕይወት ይህ ብቻ ከሆነ ይህ አስተያየት እውነት ነው፤ ልንቀበለው የሚገባ ሐቅና እውነታውን መሠረት ያደረገ አመለካከት ነው።”​— ነሐሴ 1, 1957 ገጽ 472

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ