-
የይሖዋ ወዳጅ መሆን ትችላለህለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
6. ይሖዋ ለወዳጆቹ የሚያደርጋቸው ነገሮች
ይሖዋ ወዳጆቹ ያጋጠሟቸውን ችግሮች መቋቋም እንዲችሉ ይረዳቸዋል። ቪዲዮውን ተመልከቱ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
ይሖዋ በቪዲዮው ላይ የታየችው ሴት የነበራትን አሉታዊ አስተሳሰብና ስሜት እንድታሸንፍ የረዳት እንዴት ነው?
ኢሳይያስ 41:10, 13ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦
ይሖዋ ለወዳጆቹ ሁሉ ምን እንደሚያደርግላቸው ቃል ገብቷል?
ይሖዋ ጥሩ ወዳጅ የሚሆንህ ይመስልሃል? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው?
የቅርብ ወዳጆችህ በሚያስፈልግህ ጊዜ ሁሉ ይረዱሃል። ይሖዋም ልክ እንደዚሁ ያደርጋል
-
-
ምሥራቹን ለሌሎች መናገር የምትችለው እንዴት ነው?ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
3. ይሖዋ ከአንተ ጋር ይሆናል
አንዳንዶች መስበክ ቢፈልጉም ሌሎች ለእነሱ ስለሚኖራቸው አመለካከት ወይም ስለሚሰጧቸው ምላሽ ሲያስቡ ፍርሃት ይሰማቸዋል።
የተማርከውን ነገር ለሌሎች መናገር ያስፈራሃል? እንዲህ የሚሰማህ ለምንድን ነው?
ቪዲዮውን ተመልከቱ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
በቪዲዮው ላይ የታዩት ወጣት የይሖዋ ምሥክሮች ፍርሃታቸውን እንዲያሸንፉ የረዳቸው ምንድን ነው?
ኢሳይያስ 41:10ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
መስበክ የሚያስፈራህ ከሆነ መጸለይህ የሚረዳህ እንዴት ነው?
ይህን ታውቅ ነበር?
ብዙ የይሖዋ ምሥክሮች ቀደም ሲል መቼም ቢሆን ምሥራቹን ለሌሎች መናገር እንደማይችሉ ይሰማቸው ነበር። ለምሳሌ ያህል፣ ሰርጌ የተባለ ሰው የዋጋ ቢስነት ስሜት ስለሚሰማው ሰዎችን ቀርቦ ማነጋገር ይከብደው ነበር። በኋላ ግን መጽሐፍ ቅዱስን መማር ጀመረ። እንዲህ ብሏል፦ “ፍርሃት ቢያድርብኝም የተማርኳቸውን ነገሮች ለሌሎች መናገር ጀመርኩ። በጣም የሚያስገርመው፣ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ለሌሎች መናገሬ በራስ የመተማመን ስሜቴን ከፍ አደረገልኝ። እንዲሁም የማምንባቸው አዳዲስ እውነቶች በልቤ ውስጥ ሥር እንዲሰዱ አደረጋቸው።”
-
-
ለመጠመቅ ዝግጁ ነህ?ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
6. ይሖዋ እንደሚረዳህ እምነት ይኑርህ
ይሖዋ እሱን ማስደሰት እንድትችል ይረዳሃል። ቪዲዮውን ተመልከቱ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦
በቪዲዮው ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪው ከመጠመቅ ወደኋላ ብሎ የነበረው ለምንድን ነው?
በይሖዋ ላይ ያለውን እምነት እንዲያጠናክር የረዳው ምን ማወቁ ነው?
ኢሳይያስ 41:10, 13ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
ራስህን ስትወስን የገባኸውን ቃል መጠበቅ እንደምትችል እንድትተማመን የሚያደርግህ ምንድን ነው?
-