-
አንድን ቅዱስ ምሥጢር መፍታትራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
2. (ሀ) ኢየሱስ ራሱን የገለጸው እንዴት ባለ የማዕረግ ስም ነው? (ለ) ይሖዋ “የመጀመሪያና የመጨረሻ እኔ ነኝ” ሲል ምን ማለቱ ነው? (ሐ) “የመጀመሪያውና የመጨረሻው” የሚለው የኢየሱስ የማዕረግ ስም የሚያመለክተው ምንን ነው?
2 ይሁን እንጂ አድናቆታችን ከልክ ወዳለፈ ፍርሐትና መርበትበት መድረስ አይኖርበትም። ሐዋርያው ቀጥሎ እንደሚነግረን ኢየሱስ ዮሐንስን አበረታቶት ነበር። “ቀኝ እጁንም ጫነብኝ፣ እንዲህም አለኝ፣ ‘አትፍራ፣ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ።’” (ራእይ 1:17ለ, 18ሀ) ይሖዋ በኢሳይያስ 44:6 ላይ የራሱን ደረጃ ሲገልጽ “እኔ ፊተኛ ነኝ፣ እኔም ኋለኛ ነኝ፣ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም” ብሎ ነበር።a ኢየሱስ ራሱን “ፊተኛውና መጨረሻው” ሲል ራሱን ከታላቁ ፈጣሪ ከይሖዋ ጋር ማስተካከሉ አልነበረም። አምላክ የሰጠውን የማዕረግ ስም መጠቀሙ ነበር። ይሖዋ በኢሳይያስ ላይ የተናገረው ቃል በእውነተኛ አምላክነት ደረጃው ረገድ ያለውን ብቸኛና ልዩ ቦታ የሚያመለክት ነበር። ይሖዋ የዘላለም አምላክ ሲሆን ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም። (1 ጢሞቴዎስ 1:17) ኢየሱስ ግን በራእይ ላይ ያለውን ቃል የተናገረው የተሰጠውን የማዕረግ ስም ለመጥቀስና ስለተሰጠው ልዩ ዓይነት ትንሣኤ ለማመልከት ነበር።
-
-
አንድን ቅዱስ ምሥጢር መፍታትራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
-
-
a በጥንቱ የዕብራይስጥ ጽሑፍ ውስጥ በኢሳይያስ 44:6 ላይ “የመጀመሪያ” እና “የመጨረሻ” በሚሉት ቃላት መጨረሻ ላይ “ው” የሚለው ጠቃሽ አመልካች አይገኝም። ኢየሱስ ስለራሱ በተናገረበት በጥንቱ የግሪክኛ ጽሑፍ በራእይ 1:17 ላይ ግን “ው” የሚል ጠቃሽ አመልካች አለ። ስለዚህ የሰዋስው አገባቡ እንደሚያመለክተው ራእይ 1:17 የማዕረግ ስምን የሚያመለክት ሲሆን ኢሳይያስ 44:6 ግን የይሖዋን አምላክነት የሚያመለክት ነው።
-