የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • በሐሰት ሃይማኖት ላይ ድንገተኛ ጥፋት እንደሚደርስ ተተነበየ
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • ባቢሎን ትቢያ ላይ ትጣላለች

      3. የዓለም ኃያል መንግሥት የነበረችው ባቢሎን ምን ያህል ታላቅ እንደነበረች ግለጽ።

      3 የሚከተለውን ስሜት ቀስቃሽ የሆነ መለኮታዊ መግለጫ ተመልከት:- “አንቺ ድንግል የባቢሎን ልጅ ሆይ፣ ውረጂ በትቢያም ላይ ተቀመጪ፤ የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ፣ ከዚህ በኋላ ቅልጣናምና ቅምጥል አትባይምና ያለ ዙፋን በመሬት ላይ ተቀመጪ።” (ኢሳይያስ 47:1) ባቢሎን ለበርካታ ዓመታት የዓለም ኃያል መንግሥት በመሆን በዙፋን ላይ ተቀምጣ ቆይታለች። “የመንግሥታት ክብር” ማለትም ከፍተኛ የሆነ የሃይማኖት፣ የንግድና የጦር ሠራዊት እንቅስቃሴ የሚካሄድባት ማዕከል ሆና ነበር። (ኢሳይያስ 13:​19) የባቢሎን ግዛት በስተ ደቡብ እስከ ግብጽ ድረስ ተስፋፍቶ ነበር። በተጨማሪም በ607 ከዘአበ ኢየሩሳሌምን ስትቆጣጠር በድል አድራጊነት የምታደርገውን ግስጋሴ አምላክ እንኳን ሊገታው የቻለ አይመስልም ነበር! በመሆኑም ራሷን በማንኛውም የጠላት ኃይል የማትደፈር ‘ድንግል ልጅ’ አድርጋ ቆጥራለች።b

      4. ባቢሎን ምን ይደርስባታል?

      4 ይሁን እንጂ ይህች ኩሩ “ድንግል” ዓለምን ያላንዳች ተቀናቃኝ የገዛችበት ዘመን አክትሞ ከዙፋን የምትወርድበትና የኀፍረት ማቅ ተከናንባ ‘ትቢያ ላይ የምትቀመጥበት’ ጊዜ ተቃርቦ ነበር። (ኢሳይያስ 26:​5) እንደ “ቅልጣናምና ቅምጥል” ንግሥት የሚያሞላቅቃት አይኖርም። በመሆኑም ይሖዋ የሚከተለውን ትእዛዝ ሰጥቷል:- “ወፍጮ ወስደሽ ዱቄትን ፍጪ፤ መሸፈኛሽን አውጪ ረጅሙንም ልብስሽን አውልቀሽ ጣዪው፤ ባትሽን ግለጪ፣ ወንዙን ተሻገሪ።” (ኢሳይያስ 47:2) መላውን የይሁዳ ብሔር ባሪያ አድርጋ ስትገዛ የኖረችው ባቢሎን አሁን እሷ ራሷ እንደ ባሪያ ትገዛለች! ከመንበሯ የሚያወርዷት ሜዶናውያንና ፋርሳውያን ክብርን ዝቅ የሚያደርግ የጉልበት ሥራ እንድትሠራላቸው ያስገድዷታል።

  • በሐሰት ሃይማኖት ላይ ድንገተኛ ጥፋት እንደሚደርስ ተተነበየ
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • b  በዕብራይስጥ “ድንግል የባቢሎን ልጅ” የሚለው አገላለጽ ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን ባቢሎንን ወይም የባቢሎንን ነዋሪዎች ያመለክታል። ባቢሎን የዓለም ኃያል መንግሥት ከሆነችበት ጊዜ አንስቶ አገሪቷን መበዝበዝ የቻለ አንድም የጠላት ኃይል ባለመኖሩ “ድንግል” ነበረች።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ