-
‘አምላክ በጎ ፈቃድ ያሳየበት ዘመን’የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
6. የመሲሑ አፍ በስለታም ሰይፍ መመሰሉ ምን ያመለክታል? የተሸሸገው ወይም የተሰወረውስ እንዴት ነው?
6 መሲሑ በመቀጠል የሚከተሉትን ትንቢታዊ ቃላት ተናገረ:- “አፌንም እንደ ተሳለ ሰይፍ አድርጎአል፣ በእጁ ጥላ ሰውሮኛል፤ እንደ ተሳለ ፍላጻም አድርጎኛል፣ በሰገባውም ውስጥ ሸሽጎኛል።” (ኢሳይያስ 49:2) ይሖዋ የሚልከው መሲሕ ማለትም ኢየሱስ በ29 እዘአ ምድራዊ አገልግሎቱን የሚጀምርበት ጊዜ ሲደርስ የሚናገራቸው ቃላትም ሆኑ የሚያደርጋቸው ነገሮች እንደተሳለ መሣሪያ የአድማጮቹን ልብ ሰርስረው የሚገቡ ይሆናሉ። (ሉቃስ 4:31, 32) የሚናገረው ቃልና የሚያደርጋቸው ነገሮች የይሖዋ ቀንደኛ ጠላት የሆነውን የሰይጣንንና የወኪሎቹን ቁጣ ይቀሰቅሳሉ። ሰይጣን፣ ኢየሱስን ከተወለደበት ጊዜ አንስቶ ለማጥፋት ቢሞክርም ኢየሱስ በይሖዋ ሰገባ ውስጥ እንደተሸሸገ ፍላጻ ይሆናል።a አባቱ ጥበቃ እንደሚያደርግለት ሙሉ በሙሉ መተማመን ይችላል። (መዝሙር 91:1፤ ሉቃስ 1:35) የተወሰነው ጊዜ ሲደርስ ኢየሱስ ሕይወቱን ለሰው ልጆች አሳልፎ ይሰጣል። ይሁን እንጂ ኢየሱስ ከዚህ ፍጹም በተለየ ሁኔታ ከአፉ የሚወጣ ስለታም ሰይፍ በመታጠቅ ኃያል ሰማያዊ ተዋጊ ሆኖ ብቅ የሚልበት ጊዜ ይመጣል። በዚያን ወቅት ከአፉ የሚወጣው ስለታም ሰይፍ ኢየሱስ በይሖዋ ጠላቶች ላይ ፍርድ የመበየንና የማስፈጸም ሥልጣን ያለው መሆኑን የሚያመለክት ነው።—ራእይ 1:16
-
-
‘አምላክ በጎ ፈቃድ ያሳየበት ዘመን’የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
a “ሰይጣን፣ ኢየሱስ የአምላክ ልጅ እንደሆነና አስቀድሞ በትንቢት በተነገረው መሠረት ራሱን እንደሚቀጠቅጠው (ዘፍ 3:15) በመገንዘብ ኢየሱስን ለማጥፋት ያልሸረበው ሴራ የለም። ይሁን እንጂ መልአኩ ገብርኤል ማርያም ኢየሱስን እንደምትጸንስ ባስታወቃት ጊዜ እንዲህ ብሏት ነበር:- ‘መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፣ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል፤ ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።’ (ሉቃስ 1:35) ይሖዋ ልጁን ጠብቆታል። ኢየሱስን በሕፃንነቱ ለመግደል የተደረገው ሙከራ ሁሉ ሳይሳካ ቀርቷል።”—ቅዱሳን ጽሑፎችን ጠለቅ ብሎ ማስተዋል (እንግሊዝኛ) ጥራዝ 2 ገጽ 868፣ በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀ።
-