-
“በአለቆች አትታመኑ”የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
2 ይሁዳ ለሚደርስባት ጥፋት ከራሷ ሌላ ማንንም ልትወቅስ አትችልም። ጥፋት የመጣባት ይሖዋ ስለከዳት ወይም ከሕዝቡ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን ችላ ስላለ እንደሆነ አድርጋ አምላክን ልትወነጅል አትችልም። ፈጣሪ ቃል ኪዳኑን የሚያጥፍ አምላክ አይደለም። (ኤርምያስ 31:32፤ ዳንኤል 9:27፤ ራእይ 15:4) ይሖዋ አይሁዳውያንን እንደሚከተለው ብሎ በመጠየቅ ይህን ሐቅ ጠበቅ አድርጎ ገልጾታል:- “እናታችሁን የፈታሁበት የፍችዋ ጽሕፈት የት አለ?” (ኢሳይያስ 50:1ሀ) በሙሴ ሕግ አንድ ሰው ሚስቱን በሚፈታበት ጊዜ የፍችዋን ወረቀት የመስጠት ግዴታ ነበረበት። ከዚያ በኋላ ሴቲቱ ሌላ ሰው የማግባት ነፃነት ይኖራታል። (ዘዳግም 24:1, 2) በምሳሌያዊ ሁኔታ ይሖዋ የይሁዳ እህት ለሆነችው የእስራኤል መንግሥት የፍቺ ወረቀት የሰጣት ቢሆንም ይሁዳን አልፈታትም ነበር።a በዚያም ወቅት ቢሆን ‘ባሏ’ ነበር። (ኤርምያስ 3:8, 14) በመሆኑም ይሁዳ ከአረማዊ ብሔራት ጋር ለመጎዳኘት የሚያስችል ነፃነት አልነበራትም። ‘ሴሎ [መሲሑ] እስኪመጣ ድረስ’ ይሖዋ ከይሁዳ ጋር ያለው ዝምድና እንዳለ ይቀጥላል።—ዘፍጥረት 49:10 የ1980 ትርጉም
3. ይሖዋ ሕዝቡን ‘የሸጠው’ በምን ምክንያት ነው?
3 በተጨማሪም ይሖዋ ይሁዳን እንዲህ ሲል ጠይቋታል:- “እናንተን የሸጥሁ ከአበዳሪዎች ለየትኛው ነው?” (ኢሳይያስ 50:1ለ) ይሖዋ ዕዳ ውስጥ ገብቶ ከዕዳው ለመውጣት ሲል አይሁዳውያን በባቢሎን እንዲማረኩ አያደርግም። ይሖዋ ዕዳውን ለመክፈል ሲል ልጆቹን ለአበዳሪው ለመሸጥ እንደሚገደድ ድሃ እስራኤላዊ አይደለም። (ዘጸአት 21:7) ከዚህ ይልቅ ይሖዋ ሕዝቡ በባርነት የሚገዙበት እውነተኛው ምክንያት ምን እንደሆነ ሲገልጽ እንዲህ ብሏል:- “እነሆ፣ ስለ ኃጢአታችሁ ተሸጣችኋል፣ ስለ በደላችሁም እናታችሁ ተፈትታለች [“ተሰድዳለች፣” NW ]።” (ኢሳይያስ 50:1ሐ) ይሖዋን የተዉት ራሳቸው አይሁዳውያን ናቸው እንጂ እሱ አልተዋቸውም።
-
-
“በአለቆች አትታመኑ”የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
a ይሖዋ በኢሳይያስ ምዕራፍ 50 የመጀመሪያ ሦስት ቁጥሮች ላይ የይሁዳን ብሔር በጥቅሉ እንደ ሚስቱ ነዋሪዎቿን ደግሞ በግለሰብ ደረጃ እንደ ልጆቿ አድርጎ ገልጿቸዋል።
-