የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መጽሐፍ ቅዱስ​—ትክክለኛ ትንቢት የያዘ መጽሐፍ፣ ክፍል 4
    ንቁ!—2012 | ነሐሴ
    • ክርስቶስ መከራ እንደሚቀበል ትንቢት ተነግሯል

      ትንቢት 1፦ “ለሚገርፉኝ ጀርባዬን . . . ሰጠሁ።” ​—ኢሳይያስ 50:6c

      ፍጻሜ፦ በ33 ዓ.ም. የኢየሱስ ጠላቶች የሆኑት አይሁዳውያን ኢየሱስን በሮማዊው ገዥ በጳንጥዮስ ጲላጦስ ፊት ለፍርድ አቀረቡት። አገረ ገዥው ኢየሱስ ንጹሕ ሰው መሆኑን በማወቁ ሊፈታው ሞከረ። ይሁን እንጂ ጲላጦስ፣ አይሁዳውያኑ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ኢየሱስን እንዲገድለው ስለወተወቱት ‘የጠየቁት እንዲፈጸም ፈረደላቸው’፤ ከዚያም ኢየሱስን እንዲሠቅሉት አሳልፎ ሰጣቸው። (ሉቃስ 23:13-24) ከዚያ በፊት ግን ጲላጦስ “ኢየሱስን ወስዶ ገረፈው።” (ዮሐንስ 19:1) ኢሳይያስ አስቀድሞ እንደተናገረው ኢየሱስ ‘ለሚገርፉት ጀርባውን ሰጠ’ እንጂ ለመከላከል አልሞከረም።

      ታሪክ ምን ያረጋግጣል?

      ● ሮማውያን የሞት ፍርድ የተበየነባቸውን ሰዎች ከመግደላቸው በፊት የመግረፍ ልማድ እንደነበራቸው የታሪክ መረጃዎች ያረጋግጣሉ። አንድ የማመሳከሪያ ጽሑፍ እንደገለጸው “ግርፋቱ የሚፈጸመው ቁርጥራጭ ወይም ሹል ብረቶች በተሰኩበት የጠፍር ጅራፍ ነበር። ግለሰቡ ከወገቡ በላይ ራቁቱን ሆኖ . . . ሥጋው እስኪተለተል ድረስ . . . ይገረፋል። አንዳንድ ጊዜ በግርፋቱ ብቻ ግለሰቡ ሊሞት ይችላል።” ኢየሱስ ግን የመከራው የመጀመሪያ ክፍል ከሆነው ከዚህ ከባድ ግርፋት በሕይወት ተርፏል።

  • መጽሐፍ ቅዱስ​—ትክክለኛ ትንቢት የያዘ መጽሐፍ፣ ክፍል 4
    ንቁ!—2012 | ነሐሴ
    • c የዚህ ዓረፍተ ነገር ባለቤት ክርስቶስ እንደሆነ በጥቅሱ ዙሪያ ካለው ሐሳብ መረዳት እንችላለን። ለምሳሌ ቁጥር 8 ላይ “ንጹሕ መሆኔን የሚያረጋግጥልኝ በአጠገቤ አለ” ይላል። እዚህ ላይ “ንጹሕ” የተባለው ኢየሱስ ሲሆን “በአጠገቤ አለ” የተባለው ደግሞ አምላክ ነው። ኢየሱስ ምድር ላይ በነበረበት ጊዜ ከእሱ በቀር በአምላክ ፊት ንጹሕ ወይም ጻድቅ የሆነና ኃጢአት የሌለበት አንድም ሰው አልነበረም።​—ሮም 3:23፤ 1 ጴጥሮስ 2:21, 22

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ