የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ግብዝነታቸው ተጋለጠ!
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • 8, 9. እውነተኛ ንስሐ በምን አዎንታዊ ተግባራት መደገፍ ይኖርበታል?

      8 ይሖዋ ሕዝቡ ለሠሩት ኃጢአት እንዲጾሙ ብቻ ሳይሆን ንስሐ እንዲገቡም ይፈልጋል። እንዲህ ካደረጉ ሞገሱን ያገኛሉ። (ሕዝቅኤል 18:​23, 32) ይሖዋ አንድ ሰው መጾሙ ዋጋ ሊኖረው የሚችለው ቀደም ሲል የፈጸማቸውን የኃጢአት ድርጊቶች እስከተወ ድረስ ብቻ እንደሆነ ገልጿል። ይሖዋ በመቀጠል ያቀረባቸውን እውነተኛ ዝንባሌን ለመመርመር የሚያስችሉ ጥያቄዎች ተመልከት:- “እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን? የበደልን እስራት [“ሰንሰለት፣” አ.መ.ት] ትፈቱ ዘንድ፣ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ፣ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፣ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን?”​—⁠ኢሳይያስ 58:6

      9 ሰንሰለትና ቀንበር ጨቋኝ የሆነን የባርነት አገዛዝ ጥሩ አድርገው የሚገልጹ ተስማሚ ተምሳሌቶች ናቸው። ስለዚህ ሕዝቡ በአንድ በኩል እየጾሙ በሌላ በኩል እንደነሱው ያሉ አማኞችን ከመጨቆን ይልቅ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ” የሚለውን ትእዛዝ ማክበር ይኖርባቸዋል። (ዘሌዋውያን 19:​18) በደል እየፈጸሙባቸው ያሉትንና አላግባብ በባርነት ቀንበር የያዟቸውን ሰዎች መልቀቅ አለባቸው።a ከልብ የመነጨ ለአምላክ የማደር መንፈስ ሳያሳዩና ለወንድሞቻቸው ያላቸውን ፍቅር በተግባር ሳይገልጹ እንደ ጾም ያሉትን ለታይታ የሚደረጉ ሃይማኖታዊ ተግባራት ቢፈጽሙ ዋጋ አይኖረውም። በኢሳይያስ ዘመን ይኖር የነበረው ነቢዩ ሚክያስ “ይሖዋ ከአንተ የሚሻው ምንድን ነው? ፍትሕን እንድታደርግ፣ ደግነትን እንድትወድና ልክህን አውቀህ ከአምላክህ ጋር እንድትሄድ አይደለምን?” ሲል ጽፏል።​—⁠ሚክያስ 6:​8 NW

  • ግብዝነታቸው ተጋለጠ!
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • a ይሖዋ ዕዳ ውስጥ የገቡ ሰዎች ራሳቸውን ለባርነት በመሸጥ በሌላ አባባል ተቀጥረው በመሥራት ዕዳቸውን እንዲከፍሉ ዝግጅት አድርጎ ነበር። (ዘሌዋውያን 25:​39-43) ይሁን እንጂ ሕጉ ባሪያዎች በርኅራኄ መያዝ እንዳለባቸው ይደነግጋል። ግፍ የተፈጸመባቸው ባሮች በነፃ እንዲለቀቁ ይደረጋል።​—⁠ዘጸአት 21:​2, 3, 26, 27፤ ዘዳግም 15:​12-15

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ