-
እውነተኛው አምልኮ በዓለም ዙሪያ ይስፋፋልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
መለኮታዊ ተቀባይነትን የሚያመለክት ታላቅ ብርሃን
27. በይሖዋ ‘ሴት’ ላይ የበራው የማይቋረጥ ብርሃን ምንድን ነው?
27 ይሖዋ እንደሚከተለው ብሎ በተናገረ ጊዜ በኢየሩሳሌም ላይ የሚፈነጥቀው ብርሃን ምን ያህል ደማቅ እንደሆነ አመልክቷል:- “ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ፣ አምላክሽም ክብርሽ ይሆናልና ፀሐይ በቀን ብርሃን አይሆንልሽም፣ የጨረቃም ብርሃን በሌሊት አያበራልሽም። እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ ይሆናልና፣ የልቅሶሽም ወራት ታልቃለችና ፀሐይሽ ከዚያ በኋላ አትጠልቅም ጨረቃሽም አይቋረጥም።” (ኢሳይያስ 60:19, 20) ይሖዋ ‘ለሴቲቱ’ “የዘላለም ብርሃን” ይሆንላታል። እንደ ፀሐይ ‘አይጠልቅም፣’ እንደ ጨረቃም ብርሃኑ “አይቋረጥም።”d ሞገሱን የሚያሳይበት ዘላለማዊ ብርሃኑ የአምላክ ‘ሴት’ ሰብዓዊ ወኪሎች በሆኑት ቅቡዓን ክርስቲያኖች ላይ በርቷል። ቅቡዓን ክርስቲያኖችም ሆኑ እጅግ ብዙ ሰዎች በዓለም የፖለቲካ ወይም የኢኮኖሚ መድረክ ላይ ያለው ጨለማ ሊውጠው የማይችል ደማቅ መንፈሳዊ ብርሃን ፈንጥቆላቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ ይሖዋ ቃል በገባላቸው ብሩህ ተስፋ ሙሉ ትምክህት አላቸው።—ሮሜ 2:7፤ ራእይ 21:3-5
-
-
እውነተኛው አምልኮ በዓለም ዙሪያ ይስፋፋልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
d ሐዋርያው ዮሐንስ “አዲሲቱን ኢየሩሳሌም” ማለትም ሰማያዊ ክብር የተጎናጸፉትን 144, 000ዎች አስመልክቶ ሲናገር ተመሳሳይ አገላለጽ ተጠቅሟል። (ራእይ 3:12፤ 21:10, 22-26) ‘አዲሲቷ ኢየሩሳሌም’ ሰማያዊ ሽልማታቸውን ያገኙትንና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የአምላክ ‘ሴት’ ማለትም ‘የላይኛይቱ ኢየሩሳሌም’ ዋነኛ አካል የሚሆኑትን የአምላክ እስራኤል አባላት በሙሉ የምታመለክት በመሆኑ ይህ አገላለጽ ተስማሚ ነው።—ገላትያ 4:26
-