-
በጽዮን ጽድቅ ይበቅላልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
16. በመልሶ ግንባታው ሥራ ቅቡዓን ክርስቲያኖችን በመርዳት ላይ ያሉት እነማን ናቸው? ምን ሥራስ ተሰጥቷቸዋል?
16 ይህ መጠነ ሰፊ የሆነ ሥራ ነው። በአንጻራዊ ሁኔታ ሲታይ በጣም ጥቂት የነበሩት የአምላክ እስራኤል ቀሪዎች እንዲህ ያለውን ሥራ እንዴት ሊወጡት ይችላሉ? ይሖዋ በኢሳይያስ በኩል እንዲህ ሲል ገለጸ:- “መጻተኞችም ቆመው በጎቻችሁን ያሰማራሉ፣ ሌሎች ወገኖችም አራሾችና ወይን ጠባቂዎች ይሆኑላችኋል።” (ኢሳይያስ 61:5) ምሳሌያዊዎቹ መጻተኞችና ሌሎች ወገኖች የኢየሱስ “ሌሎች በጎች” አባላት የሆኑት “እጅግ ብዙ ሰዎች” ናቸው።a (ራእይ 7:9፤ ዮሐንስ 10:11, 16) እነዚህ ሰዎች ሰማያዊ ውርሻ ያላቸው በመንፈስ ቅዱስ የተቀቡ ክርስቲያኖች አይደሉም። ከዚህ ይልቅ ገነት በምትሆነው ምድር ላይ ለዘላለም የመኖር ተስፋ ያላቸው ናቸው። (ራእይ 21:3, 4) ያም ሆኖ ይሖዋን የሚወድዱ ከመሆናቸውም በላይ መንፈሳዊ የሆነ የእረኝነት፣ የግብርናና የወይን ጠባቂነት ሥራ ተሰጥቷቸዋል። እነዚህ ተግባራት የሚናቁ ሥራዎች አይደሉም። እነዚህ ሠራተኞች በምድር ላይ ባሉት የአምላክ እስራኤል አባላት አመራር ሥር ሆነው ሰዎችን በመጠበቁ፣ በመንከባከቡና በመሰብሰቡ ሥራ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ያበረክታሉ።—ሉቃስ 10:2፤ ሥራ 20:28፤ 1 ጴጥሮስ 5:2፤ ራእይ 14:15, 16
-
-
በጽዮን ጽድቅ ይበቅላልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
a አይሁዳውያን ያልሆኑ ሰዎች ከአይሁዳውያን ጋር ወደ ኢየሩሳሌም የተመለሱ ከመሆኑም በላይ ምድሪቱን መልሶ በመገንባቱ ሥራ እንደተባበሯቸው የሚታመን በመሆኑ ኢሳይያስ 61:5 በጥንት ዘመንም ፍጻሜውን አግኝቶ ሊሆን ይችላል። (ዕዝራ 2:43-58) ይሁን እንጂ ከቁጥር 6 አንስቶ ያለው ትንቢት የአምላክ እስራኤልን ብቻ የሚያመለክት ይመስላል።
-