የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘በፈጠርሁት ለዘላለም ደስ ይበላችሁ’
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • ‘እድል በተባለ ጣዖት’ መታመን

      13, 14. የአምላክ ሕዝቦች ይሖዋን እንደተዉ የሚያሳዩ ምን ልማዶችን ይፈጽሙ ነበር? በዚህስ ሳቢያ ምን ይደርስባቸዋል?

      13 በመቀጠል የኢሳይያስ ትንቢት ይሖዋን በመተው ፊታቸውን ወደ ጣዖት አምልኮ ያዞሩትንና ለመመለስ አሻፈረኝ ያሉትን ሰዎች በማስመልከት እንዲህ ይላል:- “እናንተን ግን እግዚአብሔርን የተዋችሁትን፣ ቅዱሱንም ተራራዬን የረሳችሁትን፣ ጉድ [“ዕጣ ፈንታ፣” አ.መ.ት ] ለተባለ ጣዖትም ማዕድ ያዘጋጃችሁትን፣ እድል ለተባለ ጣዖትም የወይን ጠጅ [“ድብልቅ የወይን ጠጅ፣” አ.መ.ት ] ለመጠጥ ቁርባን የቀዳችሁትን።” (ኢሳይያስ 65:11) ወደ ኃጢአት ድርጊት የተመለሱት አይሁዳውያን ‘ዕጣ ፈንታ በተባለ ጣዖትና እድል በተባለ ጣዖት’ ፊት ማዕድና መጠጥ በማቅረብ በአረማውያን የጣዖት አምልኮ ልማዶች ተሸንፈው ወድቀዋል።b በእነዚህ አማልክት በመታመን ጥበብ የጎደለው ድርጊት የሚፈጽም ሰው ምን ይገጥመዋል?

  • ‘በፈጠርሁት ለዘላለም ደስ ይበላችሁ’
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • 15. በዛሬው ጊዜ ያሉ እውነተኛ ክርስቲያኖች በ⁠ኢሳይያስ 65:​11, 12 ላይ የሚገኘውን ማስጠንቀቂያ በተግባር ላይ የሚያውሉት እንዴት ነው?

      15 በዛሬው ጊዜ ያሉ እውነተኛ ክርስቲያኖች በ⁠ኢሳይያስ 65:​11, 12 ላይ የሚገኘውን ማስጠንቀቂያ ተግባራዊ ያደርጋሉ። ጥሩ ገድ እንዲገጥመን ሊያደርግ የሚችል ከሰው በላይ የሆነ ኃይል እንዳለ አድርገው አያምኑም። ‘እድል የተባለውን ጣዖት’ ለማስደሰት ሲሉ ቁሳዊ ንብረታቸውን አያፈስሱም። በመሆኑም ከማንኛውም ዓይነት ቁማር ይርቃሉ። ይሖዋ እነዚህን ሰዎች አስመልክቶ “እድላችሁን ለሰይፍ አደርገዋለሁ” ሲል የተናገረ በመሆኑ ለዚህ ጣዖት ያደሩ ሰዎች በመጨረሻ ሁሉንም ነገር እንደሚያጡ እርግጠኞች ናቸው።

  • ‘በፈጠርሁት ለዘላለም ደስ ይበላችሁ’
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • b የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚ የሆነው ጄሮም (በአራተኛው መቶ ዘመን እዘአ የተወለደ) ይህን ጥቅስ አስመልክቶ አስተያየት ሲሰጥ ጣዖት አምላኪዎች በዓመቱ የመጨረሻ ወር የመጨረሻ ቀን ላይ የሚያከናውኑትን አንድ ጥንታዊ ልማድ ጠቅሷል። እንዲህ ሲል ጽፏል:- “ያለፈው አሊያም መጪው ዓመት የብልጽግና ዘመን ይሆንላቸው ዘንድ መልካም ዕድል እንዲገጥማቸው በመመኘት በተለያዩ ምግቦች የተሞላ ማዕድና ጣፋጭ የሆነ ድብልቅ ወይን ጠጅ የያዘ ጽዋ ያቀርባሉ።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ