የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “እግዚአብሔር ፍቅር ነው”
    መጠበቂያ ግንብ—2003 | ሐምሌ 1
    • 16. ይሖዋ አንድ ጊዜ ኃጢአታችንን ይቅር ካለን ከዚያ በኋላ እንደ ንጹህ አድርጎ እንደሚመለከተን እርግጠኛ መሆን የምንችለው ለምንድን ነው?

      16 ከነጭ ልብስ ላይ ቆሻሻ ለማስለቀቅ ሞክረህ ታውቃለህ? አንዳንድ ጊዜ የቱንም ያህል ስትፈትገው ብትውል ቆሻሻው ሙሉ በሙሉ አይለቅ ይሆናል። ይሖዋ ይቅር ለማለት ያለውን ችሎታ ምን ብሎ እንደገለጸው ተመልከት:- ‘ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ [“በረዶ፣” አ.መ.ት ] ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች።’ (ኢሳይያስ 1:18) “አለላ” ተብሎ የተተረጎመው “ስካርሌት” የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል ደማቅ ቀይ ቀለምን ያመለክታል።a በራሳችን ጥረት የኃጢአትን እድፍ በምንም ዓይነት ማስወገድ አንችልም። ሆኖም ይሖዋ እንደ ደማቅ ቀይ ቀለም እና እንደ ደም የሆነውን ኃጢአታችንን እንደ በረዶ ወይም እንደተባዘተ ጥጥ ሊያነጣው ይችላል። በዚህም ምክንያት ይሖዋ ኃጢአታችንን አንድ ጊዜ ይቅር ካለን በቀሪው ሕይወታችን ሁሉ ከዚህ ኃጢአት እንዳልነጻን ሊሰማን አይገባም።

  • “እግዚአብሔር ፍቅር ነው”
    መጠበቂያ ግንብ—2003 | ሐምሌ 1
    • a አንድ ምሑር እንደተናገሩት ስካርሌት “የማይለቅ ቀለም ነው። ጤዛ፣ ዝናብ፣ ተደጋጋሚ እጥበት ወይም ለረጅም ጊዜ ጥቅም ላይ መዋሉ ቀለሙን አያስለቅቀውም።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ