የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የትንቢት መጽሐፍ
    ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ
    • “የጥንቷ ባቢሎን የመንግሥታት ክብር” ሆና ነበር። (ኢሳይያስ 13:​19) ባቢሎን ከፋርስ ባሕረ ሰላጤ ወደ ሜድትራንያን ባሕር በሚወስደው የንግድ መስመር ላይ የምትገኝ ታላቅ ከተማ የነበረች ሲሆን በምሥራቁና በምዕራቡ ዓለም ይካሄድ ለነበረው የባሕርና የምድር ላይ ንግድ ማዕከል ሆና ታገለግል ነበር።

      በሰባተኛው መቶ ዘመን ከዘአበ ባቢሎን ፈጽሞ ልትደፈር የማትችል የምትመስል የባቢሎን አጼያዊ ግዛት ዋና ከተማ ሆና ነበር። ከተማይቱ በኤፍራጥስ ወንዝ ላይ የተገነባች ስትሆን ወንዙ ከጠላት ወረራ የሚከላከል ሰፊና ጥልቅ የሆነ የውኃ ጉድጓድ በከተማይቱ ዙሪያ ለመሥራት ከማገልገሉም በላይ በበርካታ ቦዮች ተከፋፍሎ እንዲፈስ ተደርጎ ነበር። በተጨማሪም ከተማይቱ በጣም ግዙፍ በሆነ ድርብ የአጥር ግንብ የተከበበች ነበረች። በአጥሩም ላይ በርካታ የሆኑ የመከላከያ ግንቦች ነበሩ። የከተማይቱ ነዋሪዎች ምንም ነገር አይደርስብንም ብለው ተረጋግተው መኖራቸው የሚያስደንቅ አይደለም።

      ይሁን እንጂ በስምንተኛው መቶ ዘመን ከዘአበ የባቢሎን ክብር ታላቅ ደረጃ ላይ ከመድረሱ በፊት ነቢዩ ኢሳይያስ ባቢሎን ‘በጥፋት መጥረጊያ እንደምትጠረግ’ ተነበየ። (ኢሳይያስ 13:​19፤ 14:​22, 23) በተጨማሪም ኢሳይያስ ባቢሎን የምትወድቅበትን ሁኔታ በግልጽ ተንብዮአል። ወራሪዎቹ ባቢሎን መከላከያ አድርጋ ወደምትጠቀምባቸው ቦዮች ወንዝ ‘እንደሚያደርቁና’ ያለ መከላከያ እንደሚያስቀሯት ተናግሯል። እንዲያውም ኢሳይያስ ወራሪው “በፊቱ በሮቹ ክፍት የሚሆኑለትና መዝጊያዎቹ ሁሉ የማይዘጉበት” ታላቁ የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንደሚሆን ተንብዮአል።​— ኢሳይያስ 44:​27–45:​2 ዘ ኒው ኢንግሊሽ ባይብል

  • የትንቢት መጽሐፍ
    ለሰው ሁሉ የሚሆን መጽሐፍ
    • “ለዘላለም የሚቀመጥባት አይገኝም”

      ባቢሎን ከወደቀች በኋላ ምን ትሆናለች? ኢሳይያስ እንዲህ ሲል አስቀድሞ ተናግሯል:- “ለዘላለም የሚቀመጥባት አይገኝም። ከትውልድም እስከ ትውልድ ድረስ ሰው አይኖርባትም። ዓረባውያን ድንኳንን በዚያ አይተክሉም፣ እረኞችም መንጎታቸውን በዚያ አያሳርፉም።” (ኢሳይያስ 13:​20) ሌላው ቢቀር እንዲህ ባለ አመቺ ቦታ ላይ የተቆረቆረች ከተማ ለዘላለም ሰው የማይኖርባት ትሆናለች ብሎ መተንበይ የማይመስል ነገር መናገር ይሆናል። ኢሳይያስ ይህን ቃል የጻፈው ባቢሎን ባድማ እንደሆነች ከተመለከተ በኋላ ሊሆን ይችላልን?

      ቂሮስ ባቢሎንን እጁ ካስገባ በኋላም ቢሆን ቀድሞ ከነበራት ክብር ዝቅ ትበል እንጂ ለበርካታ መቶ ዘመናት ሰው የሚኖርባት ከተማ ሆና ቀጥላ ነበር። በሙት ባሕር ጥቅልል ውስጥ በሁለተኛው መቶ ዘመን ከዘአበ የተጻፈ ነው የሚባል ሙሉ የኢሳይያስ መጽሐፍ እንደሚገኝ ታስታውሳለህ። ይህ ጥቅልል ይገለበጥ በነበረበት ዘመን አካባቢ ፓርታውያን ባቢሎንን በግዛታቸው ሥር አስገብተው ነበር። በመጀመሪያው መቶ ዘመን እዘአ ላይ በባቢሎን ይኖሩ የነበሩ አይሁዶች ከመኖራቸውም በላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ የሆነው ጴጥሮስ ከተማይቱን ጎብኝቷት ነበር። (1 ጴጥሮስ 5:​13) በዚህ ጊዜ ላይ የኢሳይያስ የሙት ባሕር ጥቅልል ተገልብጦ ካለቀ ወደ ሁለት መቶ ዓመታት ያህል ሆኖት ነበር። ስለዚህ እስከ መጀመሪያው መቶ ዘመን እዘአ ድረስ ባቢሎን ሙሉ በሙሉ ባድማ ያልሆነች ስትሆን የኢሳይያስ መጽሐፍ ግን ተጽፎ ካለቀ ብዙ ዓመታት አልፈውታል።a

      ከጊዜ በኋላ ባቢሎን በትንቢቱ መሠረት ተራ “የድንጋይ ክምር” ሆነች። (ኤርምያስ 51:​37) ጄሮም (አራ​ተኛው መቶ ዘመን እዘአ) የተባለው ዕብራዊ ምሁር እንዳለው በእሱ ዘመን ባቢሎን “አራዊት ሁሉ” የሚፈነጩባት ሜዳ ሆና ነበር።9 ባቢሎን እስከ ዛሬም ድረስ ባድማ ነች።

      ኢሳይያስ ባቢሎን ሰው የማይኖርባት ባድማ ስትሆን በሕይወት አልነበረም። ይሁን እንጂ በአሁኑ ጊዜ በኢራቅ ከባግዳድ በስተ ደቡብ 80 ኪሎ ሜትር ርቆ የሚገኘው የዚህች በአንድ ወቅት ገናና የነበረች ከተማ ፍርስራሽ “ለዘላለም የሚቀመጥባት አይገኝም” የሚለው የኢሳይያስ ቃል በትክክል የተፈጸመ መሆኑን ይመሠክራል። ባቢሎን ታድሳ የቱሪስቶች መስህብ ብትሆን አገር ጎብኚዎች ይደሰቱ ይሆናል። ከባቢሎን ግን ‘ዘርና ትውልድ’ ለዘላለም ተቆርጧል።​— ኢሳይያስ 13:​20፤ 14:​22, 23

      ስለዚህ ነቢዩ ኢሳይያስ ማንኛውንም የወደፊት ክንውን ሊያመለክት የሚችል ግልጽ ያልሆነ ትንቢት አልተናገረም። ወይም ታሪኩ ከተፈጸመ በኋላ ትንቢት አስመስሎ አልጻፈም። እስቲ ነገሩን አስብ። አንድ አጭበርባሪ የሆነ ሰው ኃያሏ ባቢሎን ለዘላለም ባድማ እንደምትሆን በመናገር ከእርሱ ቁጥጥር ውጭ የሆነ ነገር “ተንብዮ” ራሱን ሊያጋልጥ የሚችል ነገር የሚናገርበት ምን ምክንያት አለ?

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ