ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ኢሳይያስ 24-28
ይሖዋ ሕዝቡን ይንከባከባል
ይሖዋ ልክ እንደ አንድ ለጋስ ጋባዥ የተትረፈረፈ መንፈሳዊ ምግብ ያቀርብልናል።
‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ለሕዝቦች ሁሉ ታላቅ ግብዣ ያዘጋጃል’
በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን፣ ሰዎች አብረው መመገባቸው በመካከላቸው ሰላምና ወዳጅነት እንዳለ ያመለክት ነበር
“መቅኒ የሞላባቸው ምርጥ ምግቦች እንዲሁም የተጣራና ጥሩ የወይን ጠጅ”
ምርጥ ምግቦች እና የተጣራ ጥሩ የወይን ጠጅ፣ ይሖዋ የሚያቀርብልንን እጅግ ምርጥ የሆነ መንፈሳዊ ምግብ ያመለክታሉ