የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w97 8/1 ገጽ 30-31
  • የአንባብያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የንግድ ሥራህ ምን መሥዋዕት እንድትከፍል ያስገድድሃል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • ባሮክ የኤርምያስ ታማኝ ጸሐፊ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • “የማስተዋል ስሜታችሁን ጠብቁ”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • ወንድሜን ብድር ልጠይቀውን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
w97 8/1 ገጽ 30-31

የአንባብያን ጥያቄዎች

የይሖዋ ምሥክሮች ሐቀኞች ለመሆን ስለሚጥሩና እርስ በርሳቸው ስለሚተማመኑ ገንዘብ ነክ የሆነ ጉዳይ ሲያጋጥማቸው በተገቢ ሁኔታ መዋዋል እንደሚኖርባቸው የሚሰማቸው ለምንድን ነው?

እንዲህ ማድረጋቸው ቅዱስ ጽሑፋዊና ፍቅራዊ ከመሆኑም በላይ ተግባራዊ ጠቀሜታ አለው። እንዴት? የመዋዋልን አስፈላጊነት ከሚከተሉት ምክንያቶች አንጻር እንመልከት።

አምላክ የቃል ኪዳን ሕዝቦቹ ከሆኑት እስራኤላውያን ጋር የገባው ውል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፎ ይገኛል። በተጨማሪም እውነተኛ አምላኪዎች ከሌሎች ሰዎች ጋር የገቡት ውል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግቦ እናገኛለን። በዘፍጥረት ምዕራፍ 23 ላይ አንድ ምሳሌ እናገኛለን። አብርሃም የሚወዳት ሚስቱ ሣራ በሞተች ጊዜ የመቃብር ቦታ ለማግኘት ፈለገ። በኬብሮን አቅራቢያ ከሚኖሩ ከነዓናውያን ጋር መዋዋል ጀመረ። ለፈለገው መሬት ግልጽ የሆነ ዋጋ እንደሰጣቸው ከ7-9 ያሉት ቁጥሮች ያመለክታሉ። ይህን ዋጋ የሰጠው በሕዝብ ፊት፣ በከተማይቱ በር የነበሩ ሰዎች እየሰሙት እንደሆነ ቁጥር 10 ያረጋግጥልናል። የመሬቱ ባለቤት ለአብርሃም በነጻ እንዲወስደው ሰጥቶት ነበር። ሆኖም በቁጥር 13 ላይ እንደምናነበው አብርሃም በግዥ ካልሆነ መሬቱን እንደማይወስድ ነግሮታል። ቁጥር 17, 18 እና 20 መሬቱ “በኬጢ ልጆችና በከተማይቱ በር በሚገቡ ሁሉ ፊት” ለአብርሃም የመቃብር ርስት ሆኖ እንደጸናና ልክ በተዋዋሉት መሠረት እንደተፈጸመ ያረጋግጥልናል።

ሁለቱ ተዋዋዮች እውነተኛ አምላኪዎች በሚሆኑበት ጊዜ ሁኔታው የተለየ ይሆናልን? ኤርምያስ ምዕራፍ 32 መልስ ይሰጠናል። ከቁጥር 6 ጀምረን ኤርምያስ ከአጎቱ ልጅ መሬት ለመግዛት እንዳሰበ እናነባለን። ቁጥር 9 በዋጋ እንደተስማሙ ያመለክታል። ከቁጥር 10-12 እንዲህ እናነባለን:- “በውሉም ወረቀት ላይ ፈረምሁ አተምሁትም፣ ምስክሮችንም ጠርቼ ብሩን በሚዛን መዘንሁለት። የታተመውንና የተከፈተውን የውል ወረቀት ወሰድሁ፤ የአጎቴም ልጅ አናምኤል፣ የውሉንም ወረቀት የፈረሙ ምስክሮች፣ በግዞትም ቤት አደባባይ የተቀመጡ አይሁድ ሁሉ እያዩ የውሉን ወረቀት ለመሕሤያ ልጅ ለኔርያ ልጅ ለባሮክ ሰጠሁት።”

አዎን፣ ኤርምያስ መሬት የገዛው የአምልኮ ባልደረባው ከሆነ፣ እንዲያውም የሥጋ ዘመዱ ከሆነ ሰው ቢሆንም ምክንያታዊና ሕጋዊ የሆኑ አንዳንድ ሥርዓቶች ፈጽሟል። ውሉ በሁለት ቅጂ ተዘጋጅቶ አንዱ ለማየት የፈለገ ሰው ሊያነብ በሚችልበት ቦታ ሲቀመጥ ሌላው ቅጂ ደግሞ ክፍት የሆነው ቅጂ ትክክለኛነቱ አጠራጣሪ ከሆነ ማመሳከሪያ እንዲሆን ታትሞበት እንዲቀመጥ ተደርጓል። ይህ ሁሉ የተፈጸመው ቁጥር 13 እንደሚለው “በፊታቸው” ነበር። ስለዚህ በምስክሮች ፊት የተፈጸመ ሕጋዊና ይፋ የሆነ ግብይት ነበር። ስለዚህ እውነተኛ አምላኪዎች በተረጋገጠና በሰነድ ላይ በሰፈረ ውል የሚዋዋሉት ቀደም ያሉ ቅዱስ ጽሑፋዊ ምሳሌዎችን በመከተል ነው።

በተጨማሪም ተግባራዊ ጠቀሜታ አለው። “ጊዜና አጋጣሚ ሁሉንም ይገናኛቸዋል” የሚለው አባባል ምን ያህል ትክክል እንደሆነ እናውቃለን። (መክብብ 9:​11 NW) ይህ የታመኑ ውስን ክርስቲያኖችንም ይጨምራል። ያዕቆብ 4:​13, 14 እንዲህ ሲል ገልጾታል:- “አሁንም:- ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን በዚያም ዓመት እንኖራለን እንነግድማለን እናተርፍማለን የምትሉ እናንተ፣ ተመልከቱ፣ ነገ የሚሆነውን አታውቁምና።” ስለዚህ አንድ ነገር ለመግዛት ወይም አንድ ዓይነት ሥራ ወይም አገልግሎት ለመስጠት ወይም አንድ ዓይነት ዕቃ ለሌላ ሰው ለማዘጋጀት እንዋዋል ይሆናል። ይሁን እንጂ ነገ፣ ወይም የሚቀጥለው ወር፣ ወይም የሚቀጥለው ዓመት የሚያመጣውን ማን ያውቃል? በእኛ ወይም ከእኛ ጋር በተዋዋለው ሰው ላይ አደጋ ቢደርስስ? እንዲህ ያለው ነገር ደግሞ ውሉን ማክበር አዳጋች እንዲመስል ያደርገዋል። ውል የገባንበትን ሥራ ለመሥራት ወይም አገልግሎት ለመስጠት ባንችል ወይም ሌላው ወገን ክፍያውን ለመፈጸም ወይም የበኩሉን ግዴታ ለመወጣት ፈጽሞ ባይችልስ? በጽሑፍ የሠፈረ ውል ካልኖረ ችግር ይፈጠራል። የጽሑፍ ውል ከኖረ ግን እንደነዚህ ያሉትን ችግሮች ለማስወገድ አለበለዚያም በቀላሉ ለመፍታት ይቻላል።

በተጨማሪም የተለያዩ የሕይወት ዘርፎች ተለዋዋጭና አስተማማኝ ባለመሆናቸው ምክንያት የእኛን ወይም ከእኛ ጋር የተዋዋለውን ሰው ሥራ ሌላ ሰው ተረክቦ እንዲያካሂድ የሚያስገድድ ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል መዘንጋት የለብንም። ያዕቆብ በቁጥር 14 ላይ “ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋሎት ናችሁ” ብሏል። በምክንያታዊነት ካየነው ሳናስበውም ልንሞት እንችላለን። በጽሑፍ የሠፈረ ውል ወይም ስምምነት ከኖረ አንድ ድንገተኛ ነገር ከሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች በአንዱ ላይ ቢደርስ ሌሎች የውሉን ግዴታ ለመፈጸም ይችላሉ።

ይህም ወደ ሦስተኛው ነጥብ ይመራናል። በጽሑፍ መዋዋል ለሌላው ፍቅር እንዳለን የሚያሳይ ነው። ከሁለቱ ተዋዋዮች አንዱ ቢሞት ወይም አካለ ስንኩል የሚያደርግ አደጋ ቢደርስበት ያሉበትን ግዴታዎችም ሆነ በሌሎች ላይ ያለውን ገንዘብ በጽሑፍ አስፍሮ ማቆየቱ ለአንድ ክርስቲያን ፍቅራዊ ይሆናል። የተዋዋልነው ወንድም መፈጸም የሚኖርበት ግዴታ ምን እንደሆነና ምን ጥቅም እንደሚያገኝ በግልጽ የሚያመለክት የጽሑፍ ውል መፈራረም ይህን ወንድም እንደምንጠራጠረው ሳይሆን እንደምንወደው ያመለክታል። እንዲህ ያለው ፍቅራዊ ድርጊት ከሁለቱ ፍጹማን ያልሆኑ ተዋዋዮች መካከል አንደኛው ዝርዝር ጉዳዮችን ወይም ግዴታዎቹን ቢዘነጋ የሚፈጠረውን ቅሬታና ቅያሜ በእጅጉ ይቀንሳል። ከመካከላችን ፍጹም የሆነ፣ የማይረሳ፣ ዝርዝር ጉዳዮችን ወይም የሌላውን ሰው ስሜትና ፍላጎት ፈጽሞ በተሳሳተ መንገድ የማይረዳ ሰው ይኖራልን?​—⁠ማቴዎስ 16:​5

በጽሑፍ መዋዋል ለወንድማችን፣ ለራሳችን ቤተሰብና ለጉባኤው በጠቅላላ ፍቅር እንዳለን የሚያሳይ መሆኑን የሚጠቁሙ ሌሎች መንገዶች መዘርዘር እንችላለን። ይሁን እንጂ ዝርዝር ጉዳዮችን በሙሉ ያካተተ በጽሑፍ የሰፈረ ውል ማድረግ የፍቅር መግለጫ ብቻ ሳይሆን ተግባራዊ ጥቅም ያለውና ቅዱስ ጽሑፋዊ ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ