የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ጥበበኛ ልብ አለው”—ግን ትሑት ነው
    ወደ ይሖዋ ቅረብ
    • 3 ይሖዋ ቅዱስ ነው። ትዕቢት የሚያረክስ በመሆኑ ይሖዋ እንዲህ ዓይነት ባሕርይ ሊኖረው አይችልም። (ማርቆስ 7:20-22) በተጨማሪም ነቢዩ ኤርምያስ ይሖዋን አስመልክቶ ሲናገር “አንተ በእርግጥ ታስታውሳለህ፤ እኔን ለመርዳትም ታጎነብሳለህ” ብሏል።a (ሰቆቃወ ኤርምያስ 3:20) የአጽናፈ ዓለም ሉዓላዊ ጌታ የሆነው ይሖዋ ፍጽምና የጎደለውን ኤርምያስን ለመርዳት ሲል ወደ እሱ ‘ለማጎንበስ’ ወይም ዝቅ ለማለት ፈቃደኛ መሆኑ የሚያስገርም ነው! (መዝሙር 113:7) አዎን፣ ይሖዋ ትሑት ነው። ሆኖም አምላክ ትሑት ነው ሲባል ምን ማለት ነው? ትሕትና ከጥበብ ጋር ምን ዝምድና አለው? ይህስ ለእኛ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

  • “ጥበበኛ ልብ አለው”—ግን ትሑት ነው
    ወደ ይሖዋ ቅረብ
    • a የጥንት ገልባጮች (ሶፌሪም) ይህን ጥቅስ ሲገለብጡ ወደ ታች ያጎነበሰው ይሖዋ ሳይሆን ኤርምያስ እንደሆነ አድርገው ጽፈዋል። በዚህ መንገድ የጻፉት አምላክ እንዲህ ያለውን ትሕትና የሚጠይቅ ድርጊት ይፈጽማል ብለው መጻፍ ተገቢ እንደሆነ ስላልተሰማቸው መሆን አለበት። በዚህም የተነሳ ይህ ግሩም ጥቅስ በብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ላይ በትክክል ሳይተረጎም ቀርቷል። ይሁን እንጂ ዘ ኒው ኢንግሊሽ ባይብል ኤርምያስ “አስበኝ፣ አቤቱ አስበኝ፣ ወደ እኔም ጎንበስ በል” ሲል አምላክን እንደተማጸነ በመግለጽ ይህን ጥቅስ በትክክል ተርጉሞታል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ