የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “የሚሠሯቸውን ክፉና አስጸያፊ ነገሮች ተመልከት”
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
    • ሁለተኛው ትእይንት፦ ለሐሰት አማልክት ዕጣን የሚያጥኑ 70 ሽማግሌዎች

      ሕዝቅኤል ወደ ቤተ መቅደሱ ውስጠኛ ግቢ ሲመለከት፤ ሽማግሌዎቹ በግድግዳ ላይ በተቀረጹ የሐሰት አማልክት ምስሎች ፊት ዕጣን እያጨሱ።

      11. ሕዝቅኤል በቤተ መቅደሱ መሠዊያ አቅራቢያ ወደነበረው ውስጠኛ ግቢ ሲገባ ምን የሚዘገንን ነገር ተመለከተ?

      11 ሕዝቅኤል 8:7-12⁠ን አንብብ። ሕዝቅኤል ግድግዳውን ነድሎ መሠዊያው ወደሚገኝበት ውስጠኛ ግቢ ሲገባ “መሬት ለመሬት የሚሳቡ ፍጥረታትንና የሚያስጠሉ አራዊትን ሁሉ እንዲሁም አስጸያፊ የሆኑ የእስራኤል ቤት ጣዖቶችን ሁሉ ምስል” ተመለከተ።c በግድግዳ ላይ የተቀረጹት እነዚህ ምስሎች የሐሰት አማልክትን የሚያመለክቱ ነበሩ። ቀጥሎ ደግሞ ይበልጥ የሚዘገንን ነገር አየ፤ “70 የሚሆኑ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች” “በጨለማ” ውስጥ ቆመው ለሐሰት አማልክት ዕጣን ያጥናሉ። በሙሴ ሕግ ውስጥ ጣፋጭ መዓዛ ያለው ዕጣን ማጨስ ታማኝ አምላኪዎች የሚያቀርቡትን ተቀባይነት ያለው ጸሎት ያመለክት ነበር። (መዝ. 141:2) እነዚህ 70 ሽማግሌዎች ለሐሰት አማልክት ያቀርቡ የነበረው ዕጣን ግን በይሖዋ ፊት የረከሰና የገማ ነው። ይሖዋ የሚያቀርቡትን ጸሎት እንደ መጥፎ ጠረን ተጸይፎታል። (ምሳሌ 15:8) እነዚህ ሽማግሌዎች “ይሖዋ አያየንም” በማለት ራሳቸውን ያታልሉ ነበር። ይሖዋ ግን አይቷቸዋል፤ እንዲያውም በቤተ መቅደሱ ውስጥ ምን እየሠሩ እንዳሉ ከራሱ አልፎ ለሕዝቅኤልም አሳይቶታል።

      ሰባ ሽማግሌዎች በግድግዳ ላይ በተቀረጹ የሐሰት አማልክት ምስሎች ፊት ዕጣን ሲያጨሱ።

      ይሖዋ “በጨለማ” የሚፈጸመውን አስነዋሪ ነገር በሙሉ ያያል (አንቀጽ 11⁠ን ተመልከት)

      12. “በጨለማ” ውስጥ ሳይቀር ታማኝነታችንን መጠበቅ የሚኖርብን ለምንድን ነው? በዚህ ረገድ በተለይ እነማን ጥሩ ምሳሌ መሆን ይኖርባቸዋል?

      12 ሕዝቅኤል ለሐሰት አማልክት ያጥኑ ስለነበሩት 70 እስራኤላውያን ሽማግሌዎች ከጻፈው ዘገባ ምን ትምህርት ማግኘት እንችላለን? ጸሎታችን በአምላክ ዘንድ ተሰሚነት እንዲያገኝና የምናቀርበው አምልኮ በእሱ ዓይን ንጹሕ ሆኖ እንዲገኝ ከፈለግን “በጨለማ” ውስጥም ጭምር ታማኝ ሆነን መገኘት ይጠበቅብናል። (ምሳሌ 15:29) የይሖዋ ዓይኖች የምናደርገውን ነገር ሁሉ እንደሚያዩ ማስታወስ ይኖርብናል። ይሖዋ እውን ሆኖ የሚታየን ከሆነ ብቻችንን በምንሆንበት ጊዜም እንኳ፣ እሱን እንደሚያስከፋው የምናውቀውን ነገር አናደርግም። (ዕብ. 4:13) በተለይ የጉባኤ ሽማግሌዎች በክርስቲያናዊ አኗኗር ረገድ ጥሩ ምሳሌ መሆን ይጠበቅባቸዋል። (1 ጴጥ. 5:2, 3) የጉባኤው ወንድሞችና እህቶች፣ በፊታቸው ቆሞ በስብሰባ ላይ በአምልኮ የሚመራቸው ሽማግሌ “በጨለማ” ውስጥም ማለትም ከሌሎች እይታ ውጭ በሚሆንበት ጊዜም ጭምር የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች አክብሮ ይኖራል ብለው መጠበቃቸው ተገቢ ነው።—መዝ. 101:2, 3

  • “የሚሠሯቸውን ክፉና አስጸያፊ ነገሮች ተመልከት”
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
  • “የሰው ልጅ ሆይ፣ ይህን ታያለህ?”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ