የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016 | ሰኔ
    • ሕዝቅኤል ከሃዲዋ ኢየሩሳሌም በ607 ዓ.ዓ. ከመጥፋቷ ቀደም ብሎ በውስጧ ይፈጸሙ የነበሩትን ክፉ ነገሮች ከተመለከተ በኋላ፣ ከዚህ ጥፋት በፊት ስለሚፈጸሙት ክንውኖች የሚያሳይ ራእይ ተመልክቷል። የማጥፊያ መሣሪያ የያዙ ስድስት ሰዎች በራእዩ ላይ አይቷል። በተጨማሪም ሕዝቅኤል፣ “በፍታ የለበሰ” እና “የጸሐፊ የቀለም ቀንድ የያዘ አንድ ሰው” ከእነዚህ ሰዎች ጋር ተመልክቷል። (ሕዝ. 8:6-12፤ 9:2, 3) ይህ ሰው እንዲህ ተብሏል፦ “በከተማዋ መካከል . . . እለፍ፤ በከተማዋ ውስጥ እየተፈጸሙ ባሉት አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ እያዘኑና እየቃተቱ ባሉት ሰዎች ግንባር ላይም ምልክት አድርግ።” ከዚያም የማጥፊያ መሣሪያ የያዙት ሰዎች በከተማዋ ውስጥ ምልክቱ ያልተደረገባቸውን ሰዎች በሙሉ እንዲገድሉ ታዘዙ። (ሕዝ. 9:4-7) ከዚህ ራእይ እኛ ምን ትምህርት እናገኛለን? ደግሞስ የጸሐፊ የቀለም ቀንድ የያዘው ሰው ማን ነው?

      ይህ ትንቢት የተነገረው በ612 ዓ.ዓ. ሲሆን የመጀመሪያ ፍጻሜውን ያገኘው፣ ሕዝቅኤል ራእዩን ከተመለከተ ከአምስት ዓመት በኋላ ኢየሩሳሌም በባቢሎናውያን ሠራዊት ስትጠፋ ነው። ኢየሩሳሌምን ያጠፏት አረማውያን የሆኑት ባቢሎናውያን፣ የይሖዋ ፍርድ አስፈጻሚዎች ሆነው አገልግለዋል። (ኤር. 25:9, 15-18) ይህ የሆነው ይሖዋ፣ ከሃዲ የነበሩትን ሕዝቡን ለመቅጣት በባቢሎናውያን ስለተጠቀመ ነው። ይሁን እንጂ ጥፋቱ ሁሉንም በጅምላ የሚደመስስ አልነበረም። ጻድቃን፣ ከክፉዎች ጋር እንዲጠፉ አልተደረገም። ይሖዋ፣ በከተማዋ ውስጥ በሚፈጸመው አስጸያፊ ድርጊት ያልተስማሙትን አይሁዳውያን ከጥፋቱ ለማትረፍ በፍቅር ተነሳስቶ ዝግጅት አድርጎ ነበር።

      ሕዝቅኤል፣ ምልክት በማድረጉም ሆነ በማጥፋቱ ሥራ ተካፋይ አልነበረም። ከዚህ ይልቅ ፍርድ የማስፈጸሙን ሥራ የመሩት መላእክት ነበሩ። በመሆኑም በዚህ ትንቢት አማካኝነት፣ በዓይን የማይታየውን ይኸውም በሰማይ የተከናወነውን ሁኔታ ማየት የቻልን ያህል ነው። ይሖዋ፣ ክፉዎችን እንዲያጠፉ ብቻ ሳይሆን ጻድቃንን ለይተው ከጥፋቱ እንዲያተርፉ ለመላእክቱ ተልእኮ ሰጥቷቸዋል።a

  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016 | ሰኔ
    • በዚህ ራእይ ዘመናዊ ፍጻሜ ላይ፣ የጸሐፊ የቀለም ቀንድ የያዘው ሰው ቅቡዓን ቀሪዎችን እንደሚያመለክት ከዚህ በፊት በጽሑፎቻችን ላይ ተብራርቶ ነበር። ለሚሰበከው መልእክት ቀና ምላሽ የሚሰጡ ሰዎች ከጥፋት ለመትረፍ በአሁኑ ጊዜ ምልክት እየተደረገባቸው እንደሆነ ተደርጎ ይታሰብ ነበር። ይሁን እንጂ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በዚህ ማብራሪያ ላይ ማስተካከያ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ግልጽ እየሆነ መጥቷል። በማቴዎስ 25:31-33 ላይ በተገለጸው መሠረት በሰዎች ላይ የሚፈርደው ኢየሱስ ነው። ኢየሱስ በሕይወት የሚተርፉትን በግ መሰል ሰዎች፣ ጥፋት ከሚጠብቃቸው ፍየል መሰል ሰዎች በመለየት የመጨረሻ ፍርዱን የሚሰጠው በታላቁ መከራ ወቅት ነው።

  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016 | ሰኔ
      1. በሕዝቅኤል ዘመን፣ ቃል በቃል በግንባሩ ላይ ምልክት የተደረገበት ሰው አልነበረም። በዛሬው ጊዜም ሁኔታው ተመሳሳይ ነው። ታዲያ ሰዎች ከጥፋቱ ለመትረፍ የሚያስችለው ምሳሌያዊ ምልክት እንዲደረግባቸው ምን ማድረግ ያስፈልጋቸዋል? በዛሬው ጊዜ ለሚከናወነው የስብከቱ ሥራ በጎ ምላሽ መስጠት፣ አዲሱን ክርስቲያናዊ ስብዕና መልበስ፣ ራሳቸውን ለይሖዋ መወሰንና የክርስቶስን ወንድሞች በታማኝነት መደገፍ ያስፈልጋቸዋል። (ማቴ. 25:35-40) እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉ ሰዎች፣ ከጥፋት ለመትረፍ የሚያስችላቸው ምልክት የሚደረግባቸው በመጪው ታላቅ መከራ ወቅት ይሆናል።

      2. በዘመናችን፣ የጸሐፊ የቀለም ቀንድ የያዘው ሰው የሚያመለክተው ኢየሱስ ክርስቶስን ነው፤ ከጥፋቱ በሚተርፉ ሰዎች ላይ በማይታይ ሁኔታ ምልክት የሚያደርግባቸውም እሱ ነው። እጅግ ብዙ ሕዝብ ምልክት የሚደረግባቸው፣ በጎች እንደሆኑ በታላቁ መከራ ወቅት ሲፈረድላቸው ነው። ይህም በምድር ላይ የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ያስችላቸዋል።—ማቴ. 25:34, 46b

  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016 | ሰኔ
    • a እንደ ባሮክ (የኤርምያስ ጸሐፊ)፣ ኢትዮጵያዊው ኤቤድሜሌክና ሬካባውያን ያሉት ሰዎች በግምባራቸው ላይ በዓይን የሚታይ ምልክት ባይደረግላቸውም ከጥፋቱ ተርፈዋል። (ኤር. 35:1-19፤ 39:15-18፤ 45:1-5) በሕይወት ለመትረፍ የሚያስችል ምሳሌያዊ ምልክት ተደርጎባቸዋል።

  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016 | ሰኔ
    • b ታማኝ ቅቡዓን ከጥፋቱ ለመትረፍ ይህ ምልክት አያስፈልጋቸውም። ከዚህ ይልቅ ከመሞታቸው በፊት አሊያም ታላቁ መከራ ከመፈንዳቱ ቀደም ብሎ የመጨረሻው ማኅተም ይደረግባቸዋል።—ራእይ 7:1, 3

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ