የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ሕያው ትሆናላችሁ”
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
    • “አጥንቶቻችን ደርቀዋል፤ ተስፋችንም ጨልሟል”

      6. ይሖዋ ለሕዝቅኤል የራእዩን ትርጉም የገለጠለት ምን በማለት ነበር?

      6 ቀጥሎም ይሖዋ የራእዩን ትርጉም ለሕዝቅኤል ገለጠለት፤ “እነዚህ አጥንቶች መላው የእስራኤል ቤት ናቸው” አለው። በእርግጥም ግዞተኞቹ፣ ኢየሩሳሌም ፈጽማ መውደሟን ሲሰሙ የሞቱ ያህል ሆኖ ተሰምቷቸው ነበር። በመሆኑም “አጥንቶቻችን ደርቀዋል፤ ተስፋችንም ጨልሟል። ከሌሎች ጋር ሙሉ በሙሉ ተቆራርጠናል” በማለት አልቅሰዋል። (ሕዝ. 37:11፤ ኤር. 34:20) ይሖዋ ግን ለቅሷቸውን ሲመለከት ተስፋ አስቆራጭ የሚመስለው ይህ ራእይ ለእስራኤል ብሩህ ተስፋ የሚፈነጥቅ መልእክት በውስጡ እንደያዘ ግልጽ አደረገላቸው።

  • “ሕያው ትሆናላችሁ”
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
    • 8. (ሀ) “መላው የእስራኤል ቤት” በምሳሌያዊ ሁኔታ የሞተው እንዴት ነው? (ለ) ሕዝቅኤል 37:9 እስራኤላውያን በምሳሌያዊ ሁኔታ እንዲሞቱ ምክንያት የሆነውን ነገር የሚገልጸው እንዴት ነው? (የግርጌ ማስታወሻውን ተመልከት።)

      8 አሳዛኝ የሆነው የዚህ ራእይ ገጽታ በጥንቱ የእስራኤል ብሔር ላይ የተፈጸመው እንዴት ነበር? እስራኤል በምሳሌያዊ ሁኔታ መሞት የጀመረችው በ740 ዓ.ዓ. የአሥሩ ነገድ መንግሥት በወደቀበትና ሕዝቡ በግዞት በተወሰደበት ወቅት ነበር። ከ130 ዓመት ገደማ በኋላ የይሁዳ ሕዝብ በግዞት ሲወሰድ ደግሞ “መላው የእስራኤል ቤት” ግዞተኛ ሆነ። (ሕዝ. 37:11) በዚያ ጊዜ ግዞተኞቹ በሙሉ በሕዝቅኤል ራእይ ውስጥ እንደታዩት አጥንቶች በምሳሌያዊ ሁኔታ ሞተው ነበር።a በተጨማሪም ሕዝቅኤል የተመለከተው እንዲሁ አጥንቶችን ሳይሆን ‘በጣም የደረቁ’ አጥንቶችን እንደሆነ አስታውስ፤ ይህም በምሳሌያዊ ሁኔታ ሞተው የቆዩበት ጊዜ በጣም ረጅም መሆኑን ያመለክታል። እስራኤልና ይሁዳ በግዞት የቆዩት በድምሩ ከ200 ዓመት በላይ ማለትም ከ740 እስከ 537 ዓ.ዓ. ድረስ ስለሆነ በእርግጥም ለረጅም ጊዜ ሞተው ቆይተው ነበር ሊባል ይችላል።—ኤር. 50:33

  • “ሕያው ትሆናላችሁ”
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
    • a ሕዝቅኤል በራእይ የተመለከታቸው አጥንቶች ‘የተገደሉ ሰዎች’ አጥንቶች እንጂ ተፈጥሯዊ በሆነ ሁኔታ የሞቱ ሰዎች አጥንቶች አልነበሩም። (ሕዝ. 37:9) በመጀመሪያ አሦራውያን አሥሩን ነገድ ያቀፈውን የእስራኤል መንግሥት፣ በኋላ ደግሞ ባቢሎናውያን ሁለቱን ነገድ ያቀፈውን የይሁዳ መንግሥት ድል ነስተው በግዞት በወሰዱበት ወቅት “መላው የእስራኤል ቤት” በምሳሌያዊ ሁኔታ ተገድሏል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ