የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ጅረቱ በሚፈስበት ቦታ ያለው ነገር ሁሉ በሕይወት ይኖራል”
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
    • 6. (ሀ) ራእዩ ምን አጽናኝ ተስፋ ይዟል? (ለ) ራእዩ ምን ማስጠንቀቂያ ያስተላልፋል? (የግርጌ ማስታወሻውን ተመልከት።)

      6 ሕይወት ሰጪ ውኃ። በሕዝቅኤል ራእይ ላይ ወንዙ ወደ ሙት ባሕር ገብቶ አብዛኛውን የባሕሩን ክፍል እንደፈወሰው ተገልጿል። የሙት ባሕር ውኃ ተፈውሶ እንደ ታላቁ ባሕር ማለትም እንደ ሜድትራንያን ባሕር ብዙ ዓይነት ዓሣዎች የሚርመሰመሱበት ሆኗል። እንዲያውም በሙት ባሕር ዳርቻ “ከኤንገዲ እስከ ኤንዔግላይም ድረስ” ብዙዎች ዓሣ በማጥመድ ሥራ ተሰማርተዋል፤ እነዚህ ከተሞች ተራርቀው የሚገኙ ከተሞች ሳይሆኑ አይቀሩም። መልአኩ “ጅረቱ በሚፈስበት ቦታ ያለው ነገር ሁሉ በሕይወት ይኖራል” ብሏል። ይህ ሲባል ታዲያ ከይሖዋ ቤት የወጣው ወንዝ ሙት ባሕርን ሙሉ በሙሉ ያዳርሳል ማለት ነው? አይደለም። መልአኩ ሕይወት ሰጪ የሆነው ውኃ የማይደርስባቸው ረግረጋማ የሆኑ አንዳንድ ቦታዎች እንዳሉ ገልጿል። እነዚህ ቦታዎች “ጨዋማ እንደሆኑ ይቀራሉ።”b (ሕዝ. 47:8-11) ራእዩ፣ ንጹሕ አምልኮ ሕዝቡን በመንፈሳዊ ሕያው እንዲሆኑና ጥሩ ሕይወት እንዲመሩ እንደሚያስችላቸው የሚገልጽ አጽናኝ ተስፋ ይዟል። ይሁን እንጂ ራእዩ የሚያስተላልፈው ማስጠንቀቂያም አለ፦ የይሖዋን በረከት የሚቀበሉትም ሆነ ፈውስ የሚያገኙት ሁሉም አይደሉም።

  • “ጅረቱ በሚፈስበት ቦታ ያለው ነገር ሁሉ በሕይወት ይኖራል”
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
    • b አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኞች፣ ይህ አገላለጽ አዎንታዊ ሐሳብ እንደሚያስተላልፍ ይናገራሉ፤ ምክንያቱም ምግብ ሳይበላሽ እንዲቆይ ለማድረግ የሚያገለግል ጨው ማምረት በሙት ባሕር አካባቢ ለረጅም ዘመን የቆየ አትራፊ ሥራ ነው። ይሁን እንጂ ጥቅሱ “እነዚህ ቦታዎች አይፈወሱም” በማለት በቀጥታ እንደሚናገር ልብ በል። እነዚህ ቦታዎች ከይሖዋ ቤት የሚመነጨው ሕይወት ሰጪ ውኃ ስለማይደርስባቸው ሳይፈወሱ ሕይወት አልባ እንደሆኑ ይቀራሉ። ስለዚህ በዚህ ራእይ ላይ የተጠቀሱት ረግረጋማ ቦታዎች ጨዋማ ሆነው መቅረታቸው አሉታዊ የሆነ ትርጉም የሚያስተላልፍ ሳይሆን አይቀርም።—መዝ. 107:33, 34፤ ኤር. 17:6

      c ኢየሱስ ስለ መረቡ የተናገረው ምሳሌም ተመሳሳይ መልእክት ይዟል። መረቡ ብዙ ዓሣዎችን ቢሰበስብም “ጥሩ” ሆነው የተገኙት ግን ሁሉም ዓሣዎች አይደሉም። በምሳሌው ላይ እንደተገለጸው መጥፎ መጥፎዎቹ ዓሣዎች ይጣላሉ። በዚህ መንገድ፣ ኢየሱስ ወደ ይሖዋ ድርጅት ከሚመጡት ሰዎች መካከል ጥቂት የማይባሉት ከጊዜ በኋላ ታማኝነታቸውን ሊያጓድሉ እንደሚችሉ ገልጿል።—ማቴ. 13:47-50፤ 2 ጢሞ. 2:20, 21

    • 12. (ሀ) የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ሰዎችን የጠቀማቸው እንዴት ነው? (ለ) ራእዩ ምን ማስጠንቀቂያ ይዞልናል? (የግርጌ ማስታወሻውንም ተመልከት።)

      12 ሕይወት ሰጪ ውኃ። ሕዝቅኤል “ጅረቱ በሚፈስበት ቦታ ያለው ነገር ሁሉ በሕይወት” እንደሚኖር ተነግሮታል። የእውነት ውኃ ወደ መንፈሳዊው ገነት ለመጡ ሁሉ እንዴት እንደፈሰሰላቸው ለማሰብ ሞክር። የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች በመንፈሳዊ ሁኔታ ሕያውና ጤናማ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል። ይሁን እንጂ ራእዩ፣ ለዚህ እውነት ምላሽ መስጠታቸውን የሚቀጥሉት ሁሉም ሰዎች እንዳልሆኑ የሚያሳይ ማስጠንቀቂያም ይዟል። በሕዝቅኤል ራእይ ላይ በሙት ባሕር ውስጥ ወንዙ ያልፈወሳቸው ረግረጋማና ውኃ ያቆሩ ቦታዎች እንዳሉ ተገልጾ ነበር፤ ከዚህ ጋር በሚመሳሰል ሁኔታ አንዳንድ ሰዎች የሆነ ወቅት ላይ ልባቸው በመደንደኑ ለእውነት በጎ ምላሽ መስጠታቸውን አቁመዋል።c ይህ ሁኔታ ፈጽሞ እኛ ላይ እንዲደርስ አንፈልግም!—ዘዳግም 10:16-18⁠ን አንብብ።

  • “ጅረቱ በሚፈስበት ቦታ ያለው ነገር ሁሉ በሕይወት ይኖራል”
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
    • 14, 15. (ሀ) በወንዙ ስላልተፈወሱት ረግረጋማ ቦታዎች ከሚገልጸው ሐሳብ ምን ትምህርት እናገኛለን? (ለ) ሕዝቅኤል በራእይ ያየው ወንዝ በዛሬው ጊዜ እየፈሰሰ ያለው በምን መንገድ ነው?

      14 በወንዙ ስላልተፈወሱት ረግረጋማ ቦታዎች ከሚገልጸው ሐሳብም የምናገኘው ትምህርት አለ። የይሖዋን በረከት እንዳናገኝ እንቅፋት የሚሆን ነገር ፈጽሞ ማድረግ አንፈልግም። በመንፈሳዊ ሁኔታ ታማሚ በሆነው በዚህ ዓለም ውስጥ እንዳሉት ብዙ ሰዎች ሳንፈወስ ብንቀር በጣም አሳዛኝ ይሆናል። (ማቴ. 13:15) በራእዩ ላይ ከተገለጸው በረከት የሚያስገኝ ወንዝ ተጠቃሚ በመሆናችን በእጅጉ ደስተኞች ነን። በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኘውን ንጹሕ የእውነት ውኃ ስንጠጣ፣ በስብከቱ ሥራ አማካኝነት ይህን እውነት ለሌሎች ስናካፍል እንዲሁም ታማኙ ባሪያ ሥልጠና ከሰጣቸው ሽማግሌዎች ፍቅራዊ መመሪያ፣ ማጽናኛና እርዳታ ስናገኝ ሕዝቅኤል በራእይ ያየውን ሕይወት ሰጪና ፈዋሽ የሆነ ወንዝ ማስታወሳችን አይቀርም።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ