የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዳንኤል—ክስ የቀረበበት መጽሐፍ
    የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል!
    • አይታወቅም የተባለው ንጉሥ ጉዳይ

      7. (ሀ) ዳንኤል ስለ ብልጣሶር መጥቀሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ተቺዎችን ሲያስደስታቸው የኖረው ለምንድን ነው? (ለ) ብልጣሶር ልብ ወለድ ሰው ነው የሚለው ሐሳብ ምን ገጥሞታል?

      7 ዳንኤል የባቢሎን ከተማ ስትወድቅ ንጉሥ ሆኖ ያስተዳድር የነበረው የናቡከደነፆር ‘ልጅ’ ብልጣሶር እንደሆነ ጽፏል። (ዳንኤል 5:1, 11, 18, 22, 30) ተቺዎች ብልጣሶር የሚለው ስም ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ሌላ የትም ቦታ ተጠቅሶ ስለማይገኝ ይህ አባባል ስህተት ነው እያሉ ለረጅም ጊዜ ሲተቹ ቆይተዋል። የጥንት ታሪክ ጸሐፊዎች ናቡከደነፆርን እንደተካና የባቢሎን የመጨረሻ ንጉሥ እንደነበር የሚናገሩለት ናቦኒደስ ነው። በመሆኑም በ1850 ፈርዲናንድ ሂትሲክ፣ ብልጣሶር የጸሐፊው ሐሳብ የወለደው ሰው እንደሆነ ግልጽ ነው ብለው ነበር። ነገር ግን ሂትሲክ ትንሽ የቸኮሉ አይመስልህም? ደግሞስ በዚያ የታሪካዊ መዛግብት ቁጥር እጅግ ውስን በነበረበት ዘመን የአንድ ንጉሥ ስም ተጠቅሶ አለመገኘቱ ጭራሽ እንደዚያ የሚባል ንጉሥ አልነበረም ለማለት በእርግጥ ማስረጃ ሊሆን ይችላልን? የሆነ ሆኖ በ1854 በዛሬዋ ኢራቅ ደቡባዊ ክፍል በምትገኘው ኡር በምትባለው የጥንቷ የባቢሎን ከተማ አካባቢ በተደረገው ቁፈራ አንዳንድ ትናንሽ ሞላላ ሸክላዎች ተገኙ። የሽብልቅ ቅርጽ ባላቸው ፊደላት የተጻፈባቸው እነዚህ የንጉሥ ናቦኒደስ መዛግብት ስለ “ታላቁ ልጄ ብልሳርሱር” በሚል ያቀረበውን ጸሎት ይዘው ተገኝተዋል። ተቺዎች ሳይቀሩ ይህ በዳንኤል መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሰው ብልጣሶር መሆኑን ለመቀበል ተገደዋል።

      8. ዳንኤል ብልጣሶርን በሥልጣን ላይ እንዳለ ንጉሥ አድርጎ መግለጹ እውነት መሆኑ የተረጋገጠው እንዴት ነው?

      8 ይሁንና ተቺዎች ይህ አላረካቸውም። ኤች ኤፍ ቶልበት የተባሉ አንድ ተቺ “ይህ ምንም ማስረጃ ሊሆን አይችልም” ሲሉ ጽፈዋል። በእነዚህ ሸክላዎች ላይ የተጠቀሰው ልጅ ሕፃን ልጅ ሊሆን ይችላል፤ ዳንኤል ግን የገለጸው በሥልጣን ላይ እንዳለ ንጉሥ አድርጎ ነው ብለዋል። ይሁንና የቶልበት አስተያየት በጽሑፍ ታትሞ ከወጣ ከአንድ ዓመት በኋላ ብልጣሶር ጸሐፊዎችና የቤት ውስጥ ሠራተኞች እንደነበሩት የሚገልጹ ተጨማሪ ሰሌዳዎች በቁፋሮ ተገኝተዋል። ብልጣሶር ሕፃን ልጅ አልነበረም! በመጨረሻም በአንድ ወቅት ናቦኒደስ ለተወሰኑ ዓመታት ከባቢሎን ወጣ ብሎ እንደነበር የሚገልጹ ሰሌዳዎች መገኘታቸው ጉዳዩን ይበልጥ ግልጽ አድርጎታል። በተጨማሪም እነዚሁ ሰሌዳዎች በዚህ ወቅት ናቦኒደስ በባቢሎን የነበረውን “ንግሥና” ለትልቁ ልጁ (ለብልጣሶር) “በአደራ ሰጥቶ ” እንደነበር ገልጸዋል። በእነዚህ ጊዜያት ብልጣሶር ንጉሥ ወይም በሌላ አባባል ከአባቱ ጋር የሚገዛ ተባባሪ ገዥ ነበር ለማለት ይቻላል።b

  • ዳንኤል—ክስ የቀረበበት መጽሐፍ
    የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል!
    • b ባቢሎን በወደቀችበት ጊዜ ናቦኒደስ በዚያ አልነበረም። በመሆኑም በወቅቱ ብልጣሶር ንጉሥ ተብሎ መጠራቱ ትክክል ነው። ተቺዎች ሌሎች መዛግብት ብልጣሶርን ንጉሥ የሚል ኦፊሴላዊ ማዕረግ አይሰጡትም ብለው ይከራከራሉ። የሆነ ሆኖ በዚያ ዘመን የነበሩ ሰዎች አገረ ገዥዎችን ጭምር ንጉሥ ብለው ሊጠሯቸው እንደሚችሉ የሚጠቁሙ ጥንታዊ ማስረጃዎች አሉ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ