የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ከአምላክ ዘንድ የመጣ መልእክተኛ አበረታው
    የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል!
    • 10 ዳንኤል የተመለከተው ራእይ እንዴት የሚያስገርም ነው! ዓይኑን ቀና አድርጎ ሲመለከት ያየው ተራ ሰው አልነበረም። ዳንኤል የሚከተለውን ሕያው መግለጫ ሰጥቷል:- “አካሉም እንደ ቢረሌ ይመስል ነበረ፣ ፊቱም እንደ መብረቅ ምስያ ነበረ፣ ዓይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፣ የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበረ።”—ዳንኤል 10:6

  • ከአምላክ ዘንድ የመጣ መልእክተኛ አበረታው
    የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል!
    • 13 ዳንኤል በመልክተኛውም ሰውነት ማለትም እንደ ከበረ ማዕድን ባለው የሰውነቱ አንጸባራቂ ክብር፣ ዓይን የሚያጥበረብረው የፊቱ ነፀብራቅ፣ እንደ ጦር በሚዋጉት ዓይኖቹና በሚያንጸባርቁት ፈርጣማ እጅና እግሮቹ በፍርሃት ተውጦ ነበር። ሌላው ቀርቶ እንደ ነጎድጓድ የሚያስገመግመው ድምፁም ራሱ አስፈሪ ነበር። ይህ ሁሉ ነገር ከሰው በላይ የሆነ ኃይል እንዳለው የሚያሳይ ነበር። ይህ ‘የበፍታ ልብስ የለበሰ ሰው’ በይሖዋ ፊት የሚያገለግል ከፍተኛ ሥልጣን ያለው መልአክ እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም። መልእክቱንም ያመጣው ከይሖዋ ነው።a

  • ከአምላክ ዘንድ የመጣ መልእክተኛ አበረታው
    የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል!
    • a ይህ መልአክ በስም ባይጠቀስም ስላየው ራእይ ዳንኤልን ይረዳው ዘንድ ለገብርኤል መመሪያ ሲሰጥ ድምፁ የተሰማው መልአክ ይመስላል። (ዳንኤል 8:2, 15, 16⁠ን ከዳን 12:7, 8 ጋር አወዳድር።) ከዚህም በተጨማሪ ዳንኤል 10:13 ‘ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ’ የሆነው ሚካኤል ይህንን መልአክ ሊረዳው እንደመጣ ይገልጻል። በመሆኑም ይህ ስሙ ያልተገለጸው መልአክ ከገብርኤልና ከሚካኤል ጋር በቅርብ የመሥራት መብት ያለው መልአክ መሆን ይኖርበታል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ