የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘የአምላክ ታላቅ ሥራ’ ለተግባር ያነሳሳል
    መጠበቂያ ግንብ—2002 | ነሐሴ 1
    • ለተግባር ተንቀሳቀሱ!

      4. በ33 እዘአ በዋለው የጰንጠቆስጤ ዕለት ፍጻሜውን ያገኘው የትኛው የኢዩኤል ትንቢት ነው?

      4 በኢየሩሳሌም ተገኝተው መንፈስ ቅዱስ የተቀበሉት ደቀ መዛሙርት በዚያን ዕለት ጠዋት በዓሉን ለማክበር ከተሰበሰቡት ሰዎች አንስተው የመዳንን ምሥራች ለሌሎች ለማካፈል ጊዜ አላጠፉም ነበር። የስብከት እንቅስቃሴያቸው የባቱኤል ልጅ ኢዩኤል ከስምንት መቶ ዘመናት በፊት የመዘገበው አስደናቂ ትንቢት ፍጻሜውን እንዲያገኝ አስችሏል:- “መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፣ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልምን ያልማሉ፣ ጐበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ፤ ደግሞም በዚያ ወራት በወንዶችና በሴቶች ባሪያዎች ላይ መንፈሴን አፈስሳለሁ። ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ።”​—⁠ኢዩኤል 1:​1፤ 2:​28, 29, 31፤ ሥራ 2:​17, 18, 20

      5. በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች ትንቢት የተናገሩት በምን መንገድ ነው? (የግርጌ ማስታወሻውን ተመልከት።)

      5 እንዲህ ሲባል ታዲያ አምላክ እንደ ዳዊት፣ ኢዩኤልና ዲቦራ የመሳሰሉ ወንዶችና ሴቶች ነቢያትን አስነስቶ ወደፊት የሚከናወኑ ነገሮችን እንዲተነብዩ ያደርጋል ማለት ነው? አይደለም። ክርስቲያን ‘ወንዶችና ሴቶች ልጆች እንዲሁም ባሪያዎች’ ትንቢት ይናገራሉ ሲባል ይሖዋ እስካሁን ድረስ ያደረጋቸውንና ወደፊትም የሚያደርጋቸውን ‘ታላላቅ ሥራዎች’ እንዲያውጁ በእሱ መንፈስ ይንቀሳቀሳሉ ማለት ነው። በዚህም መንገድ የልዑል ቃል አቀባይ ሆነው ያገለግላሉ።a ሆኖም የሕዝቡ ምላሽ ምን ነበር?​—⁠ዕብራውያን 1:​1, 2

  • ‘የአምላክ ታላቅ ሥራ’ ለተግባር ያነሳሳል
    መጠበቂያ ግንብ—2002 | ነሐሴ 1
    • a ሙሴና አሮን ሕዝቡን ወክለው ፈርዖንን እንዲያነጋግሩ ይሖዋ በሾማቸው ጊዜ ሙሴን “እኔ ለፈርዖን አምላክ አድርጌሃለሁ፤ ወንድምህም አሮን ነቢይ ይሆንልሃል” ብሎት ነበር። (ዘጸአት 7:​1፣ በሰያፍ የጻፍነው እኛ ነን።) አሮን ነቢይ ሆኖ ያገለገለው ወደፊት የሚፈጸሙ ነገሮችን በመተንበይ ሳይሆን የሙሴ ቃል አቀባይ በመሆን ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ