የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ጅረቱ በሚፈስበት ቦታ ያለው ነገር ሁሉ በሕይወት ይኖራል”
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
    • 3. የጥንቶቹ አይሁዳውያን በራእይ የታየው ወንዝ እውነተኛ ወንዝ ነው ብለው እንዳላሰቡ እንዴት እናውቃለን?

      3 የጥንቶቹ አይሁዳውያን በራእይ የታየው ወንዝ እውነተኛ ወንዝ ነው ብለው እንዳላሰቡ ጥያቄ የለውም። ከዚህ ይልቅ ይህ ራእይ ነቢዩ ኢዩኤል ሁለት መቶ ዓመታት ገደማ አስቀድሞ የጻፈውን፣ ንጹሕ አምልኮ መልሶ እንደሚቋቋም የሚገልጽ ሌላ ትንቢት አስታውሷቸው ይሆናል። (ኢዩኤል 3:18⁠ን አንብብ።) ግዞተኞቹ አይሁዳውያን በመንፈስ መሪነት የተጻፈውን የኢዩኤል ትንቢት ሲያነቡ ተራሮቹ ቃል በቃል “ጣፋጭ የወይን ጠጅ ያንጠባጥባሉ” ወይም “ኮረብቶቹ ወተት ያፈሳሉ” ብለው እንዳልጠበቁ የታወቀ ነው፤ ልክ እንደዚሁ “ከይሖዋም ቤት ምንጭ ይፈልቃል” ብለው አልጠበቁም። በተመሳሳይም እነዚህ አይሁዳውያን ነቢዩ ሕዝቅኤል ያየው ራእይ ስለ እውነተኛ ወንዝ የሚገልጽ እንዳልሆነ ሳይገነዘቡ አይቀሩም።a ታዲያ ይሖዋ ሊያስተላልፍ የፈለገው መልእክት ምን ነበር? ቅዱሳን መጻሕፍት የዚህን ራእይ አንዳንድ ገጽታዎች ትርጉም እንድንረዳ የሚያስችሉ ፍንጮች ይሰጡናል። በጥቅሉ ሲታይ ግን ይህ ትንቢታዊ መግለጫ የይሖዋን ፍቅር የሚያሳዩ ሦስት ዋስትናዎች ይሰጠናል። እስቲ እነዚህን ዋስትናዎች እንመልከት።

  • የይሖዋን በረከት የሚያስገኙ ወንዞች
    የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ መልሶ ተቋቋመ!
    • ኢዩኤል 3:18 ይህ ትንቢት ከቤተ መቅደሱ ስለሚፈልቅ ምንጭ ይናገራል። ይህ ምንጭ ደረቅ የሆነውን ‘የሺቲምን ሸለቆ’ ያጠጣል። ስለዚህ ኢዩኤልም ሆነ ሕዝቅኤል አንድ ወንዝ ጠፍ የሆነን ምድር ነፍስ ሲዘራበት ተመልክተዋል። በሁለቱም ትንቢቶች ላይ ወንዙ የወጣው ከይሖዋ ቤት ወይም ቤተ መቅደስ እንደሆነ ተገልጿል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ