የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w93 8/15 ገጽ 32
  • ዮናስን ዓሣ ነባሪ ውጦት ነበርን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ዮናስን ዓሣ ነባሪ ውጦት ነበርን?
  • መጠበቂያ ግንብ—1993
መጠበቂያ ግንብ—1993
w93 8/15 ገጽ 32

ዮናስን ዓሣ ነባሪ ውጦት ነበርን?

የይሖዋ ነብይ የሆነው ዮናስ በዘጠነኛው መቶ ዘመን ከዘአበ የተሰጠውን የሥራ ምድብ ትቶ በመርከብ ተሳፍሮ እንደኮበለለ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። በሜድትራያንያን ባሕር ላይ በማዕበል ውስጥ በሚጓዙበት ወቅት መርከበኞቹ ወደ ባሕሩ ውስጥ ወረወሩት። “እግዚአብሔርም ዮናስን የሚውጥ ታላቅ ዓሣ አሰናዳ፤ ዮናስም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በዓሣው ሆድ ውስጥ ነበረ።” — ዮናስ 1:​3 እስከ 2:​1

አንዳንዶች ‘ይሄማ የማይቻል ነው! አንድን ሰው ሊውጥ የሚችል ፍጥረት በባሕር ውስጥ የለም’ ይላሉ። ይሁን እንጂ ስፐርም ዌል ወይም ነጭ ትልቅ ዓሣ ነባሪ ሊውጠው ይችላል። (ታህሣስ 1992) የወጣው ናሽናል ጂኦግራፊ የተባለው መጽሔት ዌል ሻርክ የተባለውን የዓሣ ነባሪ ዓይነት በመጥቀስ ሌላ አማራጭ ያቀርባል። ይህም ዓሣ ነባሪ እስከ አሁን ድረስ ከታወቁት የሻርክ ዝርያዎች የመጨረሻው ግዙፉ ሲሆን ቁመቱ እስከ 21 ሜትር ክብደቱ ደግሞ እስከ 700 ኩንታል ይደርሳል።

“የዌል ሻርክ እንግዳ የሆኑ ምግብ የሚፈጩ የአካል ክፍሎቹ ስለ ዮናስ የሚናገረውን ታሪክ ለማስተናገድ የሚችሉ ናቸው። አንድ ሰው በጣም ትልቅ በሆነው የዌል ሻርክ አፍ ውስጥ በድንገት መግባት እንደሚችል አድርጎ ማሰብ አያስቸግረውም። የአነስተኛው ዌል ሻርክ ዋሻ የሚመስል አፍ ሁለት ዮናሶችን በቀላሉ ሊያስገባ ይችላል።”

ዌል ሻርኮች ፕላንክተንና ክሪል የሚባሉ በባሕር ላይ የሚንሳፈፉ እጽዋቶችን ይመገባሉ። እነሱም “በጉሮሮ አድርገው በጣም ሰፊና ተለጣጭ ወደሆነው በጨጓራ ውስጥ ወደሚገኘው ትልቅ አዳራሽ ይሄዳሉ።” ታዲያ አንድ ሰው ከዚያ ውስጥ እንዴት ሊወጣ ይችላል? ናሽናል ጂኦግራፊ እንዲህ ይላል:- “ሻርኮች ሳይፈልጉ የዋጧቸውን ለመፈጨት አስቸጋሪ የሆኑ ነገሮች ቀስ ብለው የማስወገድ ችሎታ አላቸው። . . . አንድ ሻርክ ጨጓራውን በአፉ በኩል ወደ ውጭ በመግፋትና የውስጡን ወደ ውጭ በመገልበጥ ጨጓራውን ባዶ ለማድረግ ይችላል። . . . ስለዚህ የሚያሙለገልግ ነገር በተሸፈነ ምንጣፍ ተንሸራትተህ ልትወጣ ትችላለህ። በዓሣው ሆድ ጡንቻዎች ምክንያት ጭብጥ ብሎ መውጣት የተሻለ ነው።”

ምንም እንኳን ዌል ሻርኮች በኒው ዮርክ ከተማ አቅራቢያ ቢገኙም ዛሬ በሜድትራኒያን ውስጥ አይገኙም። ታዲያ በዮናስ ዘመን በሜድትራኒያን ባሕር ውስጥ እነዚህ ዌል ሻርኮች ይገኙ ነበርን? ማን በእርግጠኝነት ሊያውቅ ይችላል? ይሖዋ በምን ዓይነት የባሕር ፍጥረት እንደተጠቀመ መጽሐፍ ቅዱስ ለይቶ አይገልጽም። ይሁን እንጂ የዮናስ ታሪክ እውነት መሆኑን ኢየሱስ ራሱ አረጋግጧል። — ማቴዎስ 12:​39, 40

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

Norbert Wu/Peter Arnold Inc.

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ