የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ምሕረት ስለ ማሳየት ትምህርት አግኝቷል
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
    • 8 ንጉሡም የዮናስን መልእክት ሲሰማ እርምጃ ወሰደ። አምላካዊ ፍርሃት ስላደረበትም ከዙፋኑ ወረደ፤ ልብሰ መንግሥቱንም አውልቆ እንደ ሕዝቡ ማቅ በመልበስ “በዐመድ ላይ ተቀመጠ።” ንጉሡ “ከመሳፍንቱ” ጋር በመሆን፣ ሕዝቡ በራስ ተነሳሽነት የጀመረው ጾም በመንግሥት ደረጃ ተፈጻሚነት እንዲኖረው የሚደነግግ አዋጅ አወጣ። ሕዝቡ ሁሉ፣ ሌላው ቀርቶ የቤት እንስሳትም እንኳ ማቅ እንዲለብሱ አዘዘ።b ከዚህም ሌላ ንጉሡ ሕዝቡ ክፉና ዓመፀኛ በመሆኑ የተነሳ በደለኛ መሆኑን በትሕትና አምኖ ተቀበለ። በተጨማሪም ‘እኛ እንዳንጠፋ አምላክ ከጽኑ ቍጣው ይመለስ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?’ በማለት እውነተኛው አምላክ ንስሐ መግባታቸውን ሲመለከት ሊራራላቸው እንደሚችል ያለውን ተስፋ ገለጸ።—ዮናስ 3:6-9

  • ምሕረት ስለ ማሳየት ትምህርት አግኝቷል
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
    • b ንጉሡ የወሰደው እንዲህ ያለው እርምጃ ያልተለመደ ነገር ሊመስል ቢችልም ከዚያ በፊት ተደርጎ የማያውቅ ነገር አይደለም። ግሪካዊው የታሪክ ምሁር ሄሮዶተስ፣ የጥንቶቹ ፋርሳውያን አንድ ተወዳጅ ጄኔራል በሞተ ጊዜ በሐዘን ሥነ ሥርዓቱ ላይ ከብቶቻቸውም እንዲካፈሉ እንዳደረጉ ገልጿል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ