የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ምሕረት ስለ ማሳየት ትምህርት አግኝቷል
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
    • 20 ይሖዋ ይህ ነቢይ እሱ ያልተከለውም ሆነ ያላሳደገው በአንድ ጀምበር የበቀለ ተክል በመድረቁ ማዘኑን በመግለጽ በምክንያታዊነት ያስረዳው ጀመር። እንዲህ አለው፦ “ታዲያ እኔ ቀኝና ግራቸውን ለይተው መናገር የማይችሉ፣ ከአንድ መቶ ሃያ ሺህ በላይ ሰዎችና አያሌ እንስሶች ለሚኖሩባት ለታላቋ ከተማ ለነነዌ ማዘን አይገባኝምን?”—ዮናስ 4:10, 11c

      21. (ሀ) ይሖዋ ዮናስን ምሳሌ ተጠቅሞ ምን ትምህርት አስተማረው? (ለ) የዮናስ ታሪክ ራሳችንን በሐቀኝነት እንድንመረምር ሊረዳን የሚችለው እንዴት ነው?

      21 ይሖዋ በዚህ ምሳሌ አማካኝነት ለማስተማር የፈለገውን ትልቅ ቁም ነገር አስተዋልክ? ዮናስ ያንን ተክል ለመንከባከብ ያደረገው አንዳች ነገር የለም። በሌላ በኩል ግን ይሖዋ፣ ለነነዌ ሰዎች ሕይወት ከመስጠት ባሻገር በምድር ላይ ለሚኖሩ ፍጥረታት በሙሉ እንደሚያደርገው ለእነሱም በሕይወት እንዲኖሩ የሚያስችላቸውን ነገር ሁሉ አሟልቶላቸዋል። ዮናስ 120,000 የሚሆኑት ሰዎችና እንስሶቻቸው ሕይወት ሳያሳስበው እንዴት ለአንዲት ተክል ሊቆረቆር ይችላል? እንዲህ የተሰማው የራስ ወዳድነት ዝንባሌ እንዲያድርበት ስለፈቀደ አይደለም? ደግሞም ዮናስ ለተክሉ ያዘነው ለእሱ ጥቅም ስላስገኘለት ብቻ ነው። ነነዌ ባለመጥፋቷ የተበሳጨውስ ቢሆን ቃሉ ባለመፈጸሙ ለኀፍረት እንዳይዳረግ ስለፈራ፣ በሌላ አነጋገር ራስ ወዳድ ስለነበር አይደለም? የዮናስ ታሪክ ራሳችንን በሐቀኝነት እንድንመረምር ይረዳናል። ከመካከላችን እንዲህ ዓይነቱ የራስ ወዳድነት ዝንባሌ ሊያጠቃው የማይችል ማን አለ? ይሖዋ ራስ ወዳድነትን እንድናስወግድ እንዲሁም ልክ እንደ እሱ ይበልጥ ሩኅሩኆችና መሐሪዎች እንድንሆን በትዕግሥት ስለሚያስተምረን አመስጋኞች ልንሆን ይገባናል!

  • ምሕረት ስለ ማሳየት ትምህርት አግኝቷል
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
    • c አምላክ የነነዌ ሰዎች ቀኝና ግራቸውን ለይተው መናገር እንደማይችሉ ሲገልጽ ልክ እንደ ልጆች መለኮታዊ መሥፈርቶችን ማስተዋል የማይችሉ መሆናቸውን መናገሩ ነበር።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ