የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ከአምላክ ፍቅር ሊለየን” የሚችል ነገር የለም
    ወደ ይሖዋ ቅረብ
    • 19 ይሖዋ የሌሎችን ችግር እንደ ራሱ አድርጎ የሚያይ አምላክ ነው። አንድ በዕድሜ የገፉ ታማኝ ክርስቲያን ይህን ባሕርይ ሲገልጹት “በአንተ ሥቃይ የእኔም ልብ ይታመማል” ሲሉ ተናግረዋል። ይሖዋ የእኛ ሥቃይ ይሰማዋል ማለት ነው? መጽሐፍ ቅዱስ በሕዝቡ በእስራኤላውያን ላይ የደረሰውን ሥቃይ ሲመለከት ምን እንደተሰማው ሲገልጽ “በጭንቃቸው ሁሉ እሱ ተጨነቀ” ይላል። (ኢሳይያስ 63:9) ይሖዋ እንዲሁ ችግራቸውን መመልከት ብቻ ሳይሆን እሱም አብሮ ተሠቃይቷል። “እናንተን የሚነካ ሁሉ የዓይኔን ብሌን ይነካል” በማለት ለአገልጋዮቹ የተናገረው ቃል ሥቃያቸው ምን ያህል እንደሚሰማው በግልጽ የሚያሳይ ነው።b (ዘካርያስ 2:8) የዓይን ብሌን ሲነካ ምን ያህል እንደሚያምም መገመት አያዳግትም! አዎን፣ ይሖዋ ስሜታችንን ይረዳል። ስንሠቃይ እሱም አብሮ ይሠቃያል።

  • “ከአምላክ ፍቅር ሊለየን” የሚችል ነገር የለም
    ወደ ይሖዋ ቅረብ
    • b አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ይህን ጥቅስ ሲተረጉሙ የአምላክን ሕዝብ የሚነካ የአምላክን ሳይሆን የራሱን ዓይን ወይም የእስራኤልን ሕዝብ ዓይን እንደሚነካ አድርገው ገልጸውታል። ይህ ስህተት የተፈጠረው በጥቅሱ ላይ የሰፈረው ሐሳብ አክብሮት የጎደለው እንደሆነ የተሰማቸው አንዳንድ ጸሐፊዎች ጥቅሱን በራሳቸው መንገድ ለማስተካከል በመሞከራቸው ነው። የወሰዱት የተሳሳተ እርምጃ የይሖዋ ጥልቅ የርኅራኄ ስሜት እንዲሰወር አድርጓል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ