የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሁልጊዜ የወንድማማችነት ፍቅር ይኑራችሁ!
    መጠበቂያ ግንብ—1997 | ነሐሴ 1
    • 5. ይሖዋ የሌሎችን ችግር እንደራሱ አድርጎ እንደሚመለከት እንዴት እናውቃለን?

      5 ይሖዋ በዚህ መንገድ የሌሎችን ችግር እንደራሱ ችግር አድርጎ ይመለከታልን? እንዴታ። ለምሳሌ ያህል በሕዝቡ በእስራኤል ላይ የደረሰውን መከራ በሚመለከት “በጭንቃቸው ሁሉ እርሱ ተጨነቀ” የሚል እናነባለን። (ኢሳይያስ 63:​9) ይሖዋ ችግራቸውን ከማየትም አልፎ አብሯቸው ተጨንቋል። በዘካርያስ 2:​8 (NW) ላይ የሚገኙት ይሖዋ ራሱ የተናገራቸው “የሚነካችሁ የዓይኔን ብሌን የሚነካ ነው” የሚሉት ቃላት ምን ያህል በጥልቅ እንደሚነካ ይገልጻሉ።a አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኝ ይህንን ጥቅስ በሚመለከት እንዲህ ብለዋል:- “ዓይን ከሰው ልጅ የአካል ክፍሎች ሁሉ በጣም ውስብስብ ከሆኑትና ጥንቃቄ ከሚጠይቁት መካከል አንዱ ነው፤ ከዚህ ይበልጥ ደግሞ ማየት እንችል ዘንድ የሰማይ ብርሃን ወደ ዓይናችን የሚገባበት ቀዳዳ ማለትም የዓይናችን ብሌን ከሁሉ ይበልጥ ጥንቃቄ የሚሻና በጣም ወሳኝ ክፍል ነው። ይሖዋ ለሚያፈቅራቸው ሕዝቦቹ ያለውን ጥልቅ አሳቢነት ከዚህ ይበልጥ ሊገልጽ የሚችል ምንም ነገር የለም።”

  • ሁልጊዜ የወንድማማችነት ፍቅር ይኑራችሁ!
    መጠበቂያ ግንብ—1997 | ነሐሴ 1
    • a አንዳንድ ትርጉሞች የአምላክን ሕዝቦች የሚነካ የአምላክን ዓይን እንደሚነካ ሳይሆን የእስራኤልን ወይም የራሱን ዓይን እንደሚነካ አስመስለው ተርጉመውታል። ይህ ስህተት የተፈጠረው በመካከለኛው ዘመን በኖሩትና ተቃራኒ ሐሳብ ያስተላልፋሉ ያሏቸውን ጥቅሶች በራሳቸው መንገድ በስህተት ለማስተካከል በሞከሩት ጸሐፊዎች አማካኝነት ነው። ይህን ማድረጋቸው ይሖዋ ያለው የአዛኝነት ስሜት እንዲሠወር አድርጓል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ