የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w93 11/1 ገጽ 32
  • የመከር ጊዜ!

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመከር ጊዜ!
  • መጠበቂያ ግንብ—1993
መጠበቂያ ግንብ—1993
w93 11/1 ገጽ 32

የመከር ጊዜ!

የ“ክርስትና” ታሪክ ክርስቲያናዊ ያልሆነው ለምንድን ነው? ይህን ጥያቄ የዓለም ሁኔታ የሚያሳስባቸው ብዙ ሰዎች ጠይቀውታል። ነገር ግን ኢየሱስ የዛሬ 2,000 ዓመት ገደማ በተናገረው ምሳሌ መልስ ሰጥቶበታል። እርሱም ‘በእርሻው መልካም ዘርን ስለ ዘራ ሰው’ ተናገረ። ከዚያም “ጠላቱ መጣና በስንዴው መካከል እንክርዳድን ዘርቶ ሄደ።” ዘሩ በበቀለና ባፈራ ጊዜ ሠራተኞቹ እንክርዳዱን አዩና ሊነቅሉትው ፈለጉ። ሰውየው ግን “እስከ መከር ጊዜ አብረው ይደጉ” ብሎ መለሰ። በመከር ጊዜ ስንዴው ከእንክርዳዱ እንዲለይ ይደረጋል። — ማቴዎስ 13:​24–30

ኢየሱስ ምሳሌውን ሲያብራራ “መልካሙን ዘር” ማለትም እውነተኛ ክርስቲያኖችን የዘራው ሰው እርሱ ራሱ እንደሆነ ተናገረ። ሰርጎ ገብ አስመሳይ ክርስቲያኖችን ወደ ጉባኤው በማስገባት “እንክርዳዱን” የዘራው ጠላት ሰይጣን ነበረ። ኢየሱስ እውነተኞቹም ሆነ ሐሰተኞቹ ክርስቲያኖች እስከ መከር ጊዜ ብቻ አብረው እንዲቆዩ ፈቀደ። ከዚያ በኋላ ግን ይለያሉ። — ማቴዎስ 24:​36–44

እንግዲያው “የክርስቲያን” ድርጅቶች ባለፉት መቶ ዘመናት አረመኔያዊ መሠረተ ትምህርቶችን በማስተማር፣ ብልግናን አይተው እንዳለዩ በማለፍ፣ የወረራ ጦርነቶችን በመደገፍ፣ እንዲሁም ጭካኔ የተሞላበትን ኢንኩዚሽን በማራመድ አምላክን ማዋረዳቸውን ስንረዳ መደነቅ አይገባንም። ይህን ስናይ በሰይጣን የተዘራው መጥፎው ዘር ምን እንደሆነ ለመገንዘብ እንችላለን። ሆኖም የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች አንበርዝም በማለታቸው የታሰሩ ወይም የተገደሉ መኖራቸውን ስናነብ መልካሙ ዘር ፈጽሞ እንዳልጠፋ ማስተዋል እንችላለን።

ኢየሱስ መከሩ ‘የነገሮች ሥርዓት መደምደሚያ’ ነው ብሎ ተናግሯል። በዚህ ዓለም የነገሮች ሥርዓት መደምደሚያ ዘመን ውስጥ እየኖርን ስለሆነ አሁን ያለንበት ወቅት የመከር ጊዜ መሆን ይኖርበታል! ስለሆነም በእውነተኛዎቹና በሐሰተኛዎቹ ክርስቲያኖች መካከል የሚደረገው የመለየቱ ሥራ እየተካሄደ መሆን አለበት። ዛሬ የተበታተኑ ግለሰቦች ሳይሆኑ በአንድ ቦታ የተሰባሰቡ ኢየሱስ የገለጻቸውን ብቃቶች ማለትም ለአምላክ መንግሥት የሚገዙና ስለ እርሱም የምሥራች የሚሰብኩ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ስነ ምግባርን የሚከተሉና የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት በመደገፍ አረመኔያዊ መሠረተ ትምህርቶችን የሚቃወሙ፣ የአምላክን ስም የሚያስታውቁና የዚህ ዓለም ክፍል ያልሆኑ እውነተኛ ክርስቲያኖች መገኘት አለባቸው። — ማቴዎስ 6:​33፤ 24:​14፤ ዮሐንስ 3:​20፤ 8:​32፤ 17:​6, 16

እንደዚህ ያሉ ሰዎች መኖራቸውን እናረጋግጥልሃለን! ተቀባይነት ባለው መንገድ አምላክን ልታገለግለው ትመኛለህን? እንግዲያው እነዚህን ሰዎች ፈልገህ አግኛቸው፤ አብረሃቸውም አምላክን አገልግል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ