የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘ጻድቃን እንደ ፀሐይ ደምቀው ያበራሉ’
    መጠበቂያ ግንብ—2010 | መጋቢት 15
    • 2. ኢየሱስ በተናገረው የስንዴውና የእንክርዳዱ ምሳሌ ላይ ጥሩው ዘር ምን ያመለክታል?

      2 ይሁን እንጂ ኢየሱስ ከተናገራቸው ምሳሌዎች መካከል አንደኛው ኢየሱስ በመንግሥቱ ከእሱ ጋር የሚገዙ ሰዎችን በመሰብሰቡ ሥራ ላይ ያተኮረ ነው። ይህ ምሳሌ ብዙውን ጊዜ የስንዴውና የእንክርዳዱ ምሳሌ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን በማቴዎስ ምዕራፍ 13 ላይ ይገኛል። ኢየሱስ በአንድ ሌላ ምሳሌ ላይ የተዘራው ዘር ‘የመንግሥቱ ቃል’ እንደሆነ የተናገረ ሲሆን በዚህ ምሳሌ ላይ ግን ጥሩው ዘር አንድን ለየት ያለ ነገር ማለትም ‘የመንግሥቱን ልጆች’ እንደሚያመለክት ገልጿል። (ማቴ. 13:19, 38) እነዚህ ልጆች የመንግሥቱ ተገዢዎች ሳይሆኑ የመንግሥቱ “ልጆች” ወይም ወራሾች ናቸው።—ሮም 8:14-17፤ ገላትያ 4:6, 7⁠ን አንብብ።

  • ‘ጻድቃን እንደ ፀሐይ ደምቀው ያበራሉ’
    መጠበቂያ ግንብ—2010 | መጋቢት 15
    • 4. (ሀ) በምሳሌው ላይ የተገለጸው ሰው ማነው? (ለ) ኢየሱስ ይህን ዘር በመዝራቱ ሥራ መካፈል የጀመረው መቼና እንዴት ነው?

      4 በእርሻው ላይ ጥሩ ዘር የዘራው ሰው ማነው? ኢየሱስ ቆየት ብሎ የምሳሌውን ትርጉም ለደቀ መዛሙርቱ ባብራራላቸው ጊዜ “ጥሩውን ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው” በማለት መልሱን ተናግሯል። (ማቴ. 13:37) “የሰው ልጅ” ተብሎ የተጠራው ኢየሱስ ምድራዊ አገልግሎቱን ባከናወነባቸው ሦስት ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ እርሻውን አለስልሶ ለዘር አዘጋጅቷል። (ማቴ. 8:20፤ 25:31፤ 26:64) ከዚያም በ33 ዓ.ም. ከተከበረው የጴንጤቆስጤ ዕለት አንስቶ ጥሩ ዘር የሆኑትን ‘የመንግሥቱን ልጆች’ መዝራት ጀመረ። ይህ የመዝራት ሥራ የተከናወነው ኢየሱስ የይሖዋ ወኪል ሆኖ በደቀ መዛሙርቱ ላይ መንፈስ ቅዱስን ማፍሰስ በጀመረበትና የአምላክ ልጆች አድርጎ በቀባቸው ጊዜ እንደነበረ ግልጽ ነው።b (ሥራ 2:33) ከጊዜ በኋላ ጥሩው ዘር ማለትም ስንዴው አድጎ ጎመራ። ስለዚህ ጥሩ ዘር የሚዘራበት ዓላማ ከኢየሱስ ጋር በመንግሥቱ ተባባሪ ወራሾችና ገዥዎች የሚሆኑት ሰዎች ቁጥር እስኪሟላ ድረስ እነሱን በጊዜ ሂደት ለመሰብሰብ ነው።

  • ‘ጻድቃን እንደ ፀሐይ ደምቀው ያበራሉ’
    መጠበቂያ ግንብ—2010 | መጋቢት 15
    • 5. በምሳሌው ላይ የተገለጸው ጠላት ማን ነው? በእንክርዳዱስ የተመሰሉት እነማን ናቸው?

      5 ጠላት የተባለው ማን ነው? እንክርዳድ የተባሉትስ እነማን ናቸው? ኢየሱስ ጠላት የተባለው “ዲያብሎስ ነው” በማለት ተናግሯል። እንክርዳዶቹ ደግሞ “የክፉው ልጆች” እንደሆኑ ተገልጿል። (ማቴ. 13:25, 38, 39) እንክርዳድ መርዛማ እህል ሲሆን በቡቃያነት ደረጃ ከስንዴ ጋር በጣም ይመሳሰላል። የመንግሥቱ ልጆች እንደሆኑ ቢናገሩም እውነተኛ ፍሬ የማያፈሩ አስመሳይ ክርስቲያኖች በእንክርዳድ መመሰላቸው ምንኛ የተገባ ነው! እንደ እውነቱ ከሆነ፣ የክርስቶስ ተከታይ እንደሆኑ የሚናገሩት እነዚህ ግብዝ ክርስቲያኖች የሰይጣን ዲያብሎስ ‘ዘር’ ክፍል ናቸው።—ዘፍ. 3:15

  • ‘ጻድቃን እንደ ፀሐይ ደምቀው ያበራሉ’
    መጠበቂያ ግንብ—2010 | መጋቢት 15
    • 7. አንዳንድ ስንዴዎች ተቀይረው እንክርዳድ ሆነው ነበር? አብራራ።

      7 ኢየሱስ እዚህ ምሳሌ ላይ ስንዴው ተቀይሮ እንክርዳድ ይሆናል አላለም፤ ከዚህ ይልቅ እሱ የተናገረው በስንዴው መካከል እንክርዳድ እንደተዘራ ነው። በመሆኑም ይህ ምሳሌ ከእውነት የወጡትን እውነተኛ ክርስቲያኖች የሚያመለክት አይደለም። ከዚህ ይልቅ ሰይጣን ክፉ ሰዎች ወደ ክርስቲያን ጉባኤ ሰርገው እንዲገቡ በማድረግ ሆን ብሎ ጉባኤውን ለመበከል የሚያደርገውን ጥረት ያመለክታል። የመጨረሻ ሐዋርያ የነበረው ዮሐንስ ዕድሜው በገፋበት ወቅት ክህደቱ በግልጽ መታየት ጀምሮ ነበር።—2 ጴጥ. 2:1-3፤ 1 ዮሐ. 2:18

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ