-
ምሥራቹን የሚሰብኩ ሰዎች—ሰባኪዎች ራሳቸውን በፈቃደኝነት አቀረቡየአምላክ መንግሥት እየገዛ ነው!
-
-
የተደበቀ ውድ ሀብት ሲያገኝ በደስታ እንደሚሞላ ሰው ክርስቲያኖችም የመንግሥቱን እውነት በማግኘታቸው በጣም ይደሰታሉ (አንቀጽ 20ን ተመልከት)
20. ኢየሱስ ስለ ተደበቀ ውድ ሀብት የተናገረው ምሳሌ፣ ተከታዮቹ አስቀድመው መንግሥቱን መፈለጋቸውን እንዲቀጥሉ ለተሰጣቸው ምክር ምን ምላሽ እንደሚሰጡ የሚጠቁመው እንዴት ነው?
20 ኢየሱስ፣ ተከታዮቹ አስቀድመው መንግሥቱን መፈለጋቸውን እንዲቀጥሉ ለተሰጣቸው ምክር ምን ምላሽ እንደሚሰጡ ያውቅ ነበር። ስለ አንድ የተደበቀ ውድ ሀብት የተናገረውን ምሳሌ እንመልከት። (ማቴዎስ 13:44ን አንብብ።) በምሳሌው ላይ የተገለጸው ሠራተኛ የዕለት ተዕለት ሥራውን እያከናወነ ሳለ የተደበቀ ውድ ሀብት አገኘ፤ ያገኘው ነገር ምን ያህል ዋጋ እንዳለው ለማወቅ ጊዜ አልወሰደበትም። ታዲያ ምን አደረገ? “ከመደሰቱም የተነሳ ሄዶ ያለውን ሁሉ በመሸጥ እርሻውን ገዛው።” ይህ ምሳሌ ምን ትምህርት ይዞልናል? የመንግሥቱን እውነት ስናገኝና ያለውን ዋጋ ስንገነዘብ ከዚህ መንግሥት ጋር ለተያያዙ ነገሮች ተገቢውን ቦታ ይኸውም በሕይወታችን ውስጥ አንደኛውን ቦታ ለመስጠትና ይህን ማድረጋችንን ለመቀጠል እንጥራለን፤ ለዚህም ስንል ምንም ቅር ሳይለን አስፈላጊውን መሥዋዕት ሁሉ እንከፍላለን።d
-
-
ምሥራቹን የሚሰብኩ ሰዎች—ሰባኪዎች ራሳቸውን በፈቃደኝነት አቀረቡየአምላክ መንግሥት እየገዛ ነው!
-
-
d ኢየሱስ፣ ከፍተኛ ዋጋ ያለውን ዕንቁ ለመፈለግ ስለሄደ ተጓዥ ነጋዴ የተናገረው ምሳሌም ተመሳሳይ ትምህርት ይዟል። ነጋዴው ዕንቁውን ሲያገኘው ያለውን ሁሉ ሸጦ ገዛው። (ማቴ. 13:45, 46) ሁለቱ ምሳሌዎች የመንግሥቱን እውነት የምንማርበት መንገድ ሊለያይ እንደሚችልም ያሳያሉ። አንዳንዶች እውነትን የሚያገኙት በአጋጣሚ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ፈልገው ያገኙታል። እውነትን ያገኘንበት መንገድ ምንም ይሁን ምን በሕይወታችን ውስጥ መንግሥቱን ለማስቀደም ስንል መሥዋዕት ለመክፈል ፈቃደኞች ነን።
-