-
ንጉሡ ተከታዮቹን በመንፈሳዊ ያጠራቸዋልየአምላክ መንግሥት እየገዛ ነው!
-
-
መረቡ፣ በሰው ዘር ባሕር ውስጥ የሚከናወነውን የመንግሥቱን ስብከት ሥራ ያመለክታል (አንቀጽ 18ን ተመልከት)
18 ‘መረቡን ወደ ባሕር መጣል።’ መረቡ፣ በሰው ዘር ባሕር ውስጥ የሚከናወነውን የመንግሥቱን ስብከት ሥራ ያመለክታል። “የተለያየ ዓይነት ዓሣ” መሰብሰብ። ምሥራቹ የተለያዩ ዓይነት ሰዎችን ይኸውም እርምጃ ወስደው እውነተኛ ክርስቲያን የሚሆኑ ግለሰቦችንና መጀመሪያ ላይ ለመልእክቱ የተወሰነ ፍላጎት ቢያሳዩም ከእውነተኛው አምልኮ ጎን ለመቆም እርምጃ የማይወስዱ በርካታ ሰዎችን ይስባል።e “ጥሩ ጥሩውን እየለዩ በዕቃ ውስጥ” ማስቀመጥ። ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች በዕቃ ወደተመሰሉት የክርስቲያን ጉባኤዎች የሚሰበሰቡ ሲሆን በዚያም ለይሖዋ ንጹሕ አምልኮ ያቀርባሉ።“መጥፎ መጥፎውን” ዓሣ መጣል። በመጨረሻዎቹ ቀናት በሙሉ ክርስቶስና መላእክት፣ “ክፉዎችን ከጻድቃን” ሲለዩ ቆይተዋል።f ይህም ትክክለኛ የልብ ዝንባሌ የሌላቸው ሰዎች ማለትም የተሳሳቱ እምነቶችንና ልማዶችን ለመተው ፈቃደኛ ያልሆኑ ግለሰቦች ጉባኤዎችን እንዳይበክሉ ለማድረግ አስችሏል!g
-
-
ንጉሡ ተከታዮቹን በመንፈሳዊ ያጠራቸዋልየአምላክ መንግሥት እየገዛ ነው!
-
-
f ጥሩውን ዓሣ ከመጥፎው ዓሣ የመለየቱ ሥራ በጎችን ከፍየሎቹ ከመለየቱ ሥራ ጋር አንድ አይደለም። (ማቴ. 25:31-46) በጎቹ ከፍየሎቹ የሚለዩት ማለትም የመጨረሻው ፍርድ የሚከናወነው በመጪው ታላቅ መከራ ወቅት ነው። እስከዚያው ድረስ ግን በመጥፎ ዓሣ የተመሰሉት ሰዎች ወደ ይሖዋ መመለስና በዕቃ በተመሰሉት ጉባኤዎች ውስጥ መሰብሰብ ይችላሉ።—ሚል. 3:7
-