-
ጉባኤው እየተጠናከረ ይሂድመጠበቂያ ግንብ—2007 | ሚያዝያ 15
-
-
10. በማቴዎስ 18:15-17 መሠረት ከበድ ያሉ አለመግባባቶች መፈታት ያለባቸው እንዴት ነበር?
10 ኢየሱስ ይህ ዓይነቱ ዝግጅት እንደሚኖር ጠቁሞ ነበር። በማቴዎስ 18:15-17 ላይ የሚገኘው ዘገባ እንደሚገልጸው አንድ የአምላክ አገልጋይ ሌላውን በሚበድልበት ወቅት በሁለት ክርስቲያኖች መካከል አለመግባባት ይፈጠር ይሆናል። በዚህ ጊዜ የተበደለው ወገን ወደ ሌላው ግለሰብ ሄዶ ሁለቱ ብቻ ባሉበት ‘ጥፋቱን ሊነግረው’ ይገባል። አለመግባባቱ በዚህ መንገድ ሊፈታ ካልቻለ ግን ጉዳዩን የሚያውቁ አንድ ወይም ሁለት ሰዎች መጥራት ይቻላል። ይህ ሁሉ ተደርጎም ጉዳዩ ባይፈታስ? ኢየሱስ “እነርሱን ባይሰማ ለቤተ ክርስቲያን ንገር፤ ቤተ ክርስቲያንንም ባይሰማ እንደ አሕዛብና እንደ ቀረጥ ሰብሳቢ ቊጠረው” ብሏል። ኢየሱስ ይህንን በተናገረበት ወቅት አይሁዳውያን ‘የአምላክ ጉባኤ’ ስለነበሩ ሐሳቡ በዋነኝነት የሚሠራው ለእነርሱ ነበር።a ይሁን እንጂ የክርስቲያን ጉባኤ ከተቋቋመ በኋላ ኢየሱስ የሰጠው መመሪያ ለዚህ ጉባኤም ይሠራል። ይህም የአምላክ ሕዝቦች በግለሰብ ደረጃ እንዲጠናከሩና መመሪያ እንዲያገኙ የሚረዳ የጉባኤ ዝግጅት እንደሚኖር የሚጠቁም ሌላው ማስረጃ ነው።
11. ሽማግሌዎች ችግሮችን በመፍታት ረገድ ምን ሚና ይጫወቱ ነበር?
11 ሽማግሌዎች ወይም የበላይ ተመልካቾች ችግሮችን በመፍታት አሊያም ኃጢአት ከመሥራት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በመመልከት ረገድ በአካባቢው የነበረውን ጉባኤ ወክለው ማገልገላቸው ተገቢ ነው። ይህም በቲቶ 1:9 ላይ ሽማግሌዎች ሊያሟሏቸው እንደሚገቡ ከተገለጹት ብቃቶች ጋር የሚስማማ ነው። በእነዚያ ጉባኤዎች ውስጥ የሚገኙት ሽማግሌዎችም ሆኑ ‘ያልተስተካከለውን ነገር እንዲያስተካክል’ ጳውሎስ ወደ ጉባኤዎች የላከው ቲቶ ፍጹም እንዳልነበሩ አይካድም። (ቲቶ 1:4, 5) በዛሬው ጊዜም ወንድሞች ሽማግሌ ሆነው ለመሾም ብቁ መሆናቸውን ለመወሰን፣ እምነት እንዳላቸውና ለአምላክ ያደሩ እንደሆኑ መመልከት ያስፈልጋል። በመሆኑም በጉባኤ ውስጥ ያሉ ሌሎች ክርስቲያኖች በዚህ ዝግጅት አማካኝነት የተሾሙት ወንድሞች በሚሰጧቸው መመሪያም ሆነ አመራር ለመተማመን የሚያበቃ ምክንያት አላቸው።
-
-
ጉባኤው እየተጠናከረ ይሂድመጠበቂያ ግንብ—2007 | ሚያዝያ 15
-
-
a የመጽሐፍ ቅዱስ ምሑር የሆኑት አልበርት ባርንስ እንደተናገሩት ኢየሱስ ለጉባኤ ወይም “ለቤተ ክርስቲያን ንገር” ሲል “እንዲህ ያሉ ጉዳዮችን ለመመልከት ሥልጣን ያላቸውን ሰዎች ማለትም የቤተ ክርስቲያን ተወካዮችን” ማመልከቱ ሊሆን ይችላል። “በአይሁዳውያን ምኩራብ ውስጥ እንዲህ ዓይነት ጉዳዮችን ለመመልከት ዳኞች ሆነው የሚያገለግሉ ሽማግሌዎች ነበሩ።”
-