-
ወንድምህን ገንዘብ ልታደርገው ትችላለህመጠበቂያ ግንብ—1999 | ጥቅምት 15
-
-
5, 6. ከጥቅሱ አገባብ አንጻር ማቴዎስ 18:15 የሚያመለክተው ምን ዓይነት ኃጢአትን ነው? ይህንን እንደሚያመለክትስ የሚያሳየው ምንድን ነው?
5 እንደ እውነቱ ከሆነ ኢየሱስ የሰጠው ምክር ከበድ ላሉ ጉዳዮች የሚሠራ ነው። ኢየሱስ “ወንድምህም ቢበድልህ [“ኃጢአት ቢሠራ፣” NW]” በማለት ተናግሯል። ሰፋ አድርገን ከተመለከትነው “ኃጢአት” የሚለው አነጋገር ማንኛውንም ዓይነት ስህተት ወይም ጥፋት ሊያመለክት ይችላል። (ኢዮብ 2:10፤ ምሳሌ 21:4፤ ያዕቆብ 4:17) ይሁን እንጂ ከጥቅሱ ዙሪያ ያሉት ሐሳቦች እንደሚያመለክቱት ኢየሱስ ኃጢአት በማለት የጠቀሰው ከበድ ያለ ኃጢአትን የሚያመለክት መሆን አለበት። ግለሰቡን “እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ” ሊያስቆጥር የሚችል ክብደት ያለው ስህተት ነው። ታዲያ ይህ ሐረግ ምን ነገርን የሚያመለክት ነው?
6 እነዚህን የኢየሱስ ቃላት ያዳምጡ የነበሩት የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት የአገራቸው ሰዎች ከአሕዛብ ጋር ምንም ዓይነት ማኅበራዊ ግንኙነት እንደማያደርጉ ያውቁ ነበር። (ዮሐንስ 4:9፤ 18:28፤ ሥራ 10:28) እንዲሁም የአይሁድ ተወላጅ ቢሆኑም እንኳ ሕዝቡን የሚጨቁኑትን ቀረጥ ሰብሳቢዎች ሙሉ በሙሉ ይርቋቸው ነበር። እንደ እውነቱ ከሆነ ማቴዎስ 18:15-17 ላይ የሠፈረው መግለጫ የሚያመለክተው በቀላሉ ይቅር ብለህ ልትረሳው የምትችለውን ቅሬታ ወይም ቅያሜ ሳይሆን ከበድ ያሉ ኃጢአቶችን ነው።—ማቴዎስ 18:21, 22a
-
-
ወንድምህን ገንዘብ ልታደርገው ትችላለህመጠበቂያ ግንብ—1999 | ጥቅምት 15
-
-
a በማክሊንቶክ እና ስትሮንግስ የተዘጋጀው ሳይክለፒዲያ እንዲህ ይላል:- “በአዲስ ኪዳን ውስጥ የተጠቀሱት ቀራጮች [ቀረጥ ሰብሳቢዎች] ከአረመኔዎች ጋር በመቀራረብ የረከሱ፣ ለጨቋኞች ቀኝ እጅ ሆነው ለማገልገል ራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ ከዳተኞችና ከሃዲዎች እንደሆኑ ተደርገው ይቆጠሩ ነበር። ከኃጢአተኞች ጋር በአንድ ዓይን ይታዩ ነበር። . . . በዚህ መንገድ የተገለሉ ሰዎች በመሆናቸው ጨዋ የሆኑ ሰዎች ጨርሶ ወደ እነርሱ አይቀርቡም ነበር። እነርሱን ወዳጅ ወይም ጓደኛ በማድረግ የሚቀርቧቸው ልክ እንደ እነርሱ ኅብረተሰቡ ያገለላቸው ሰዎች ብቻ ነበሩ።”
-