የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • በዛሬው ጊዜ አምላክን በመሐሪነቱ ምሰሉት
    መጠበቂያ ግንብ—1991 | ሚያዝያ 15
    • 2. ኢየሱስ በማቴዎስ 18:15-17 ላይ ከባድ ኃጢአትን በተመለከተ ምን ምክር ሰጠ?

      2 መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አምላክ አስተሳሰብ ጠለቅ ያለ ማስተዋል ይሰጠናል። ለምሳሌ አንድ ሰው በእኛ ላይ ኃጢአት ቢሠራ ልናደርጋቸው ስለሚገቡን ነገሮች እንኳ ሳይቀር ጥልቅ ማስተዋል ይሰጠናል። ኢየሱስ ከጊዜ በኋላ ክርስቲያን የበላይ ተመልካቾች ለሚሆኑት ሐዋርያቱ “ወንድምህም ቢበድልህ፣ ሄደህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ውቀሰው፤ ቢሰማህ ወንድምህን ገንዘብ አደረግኸው” ብሏቸው ነበር። እዚህ ላይ የተገለጸው በደል እንዲሁ ተራ የግል ስህተት አልነበረም፤ እንደ ማጭበርበር ወይም ስም ማጥፋት ያለውን ከባድ ኃጢአት የሚመለከት ነበር። ይህ እርምጃ ለችግሩ መፍትሄ ካላመጣና ምስክሮች የሚገኙ ከሆነ በደል የተፈጸመበት ሰው በደሉን ለማረጋገጥ ምሥክሮቹን ይዟቸው መሄድ እንደሚገባው ኢየሱስ ተናግሯል። ይህ በመጨረሻ ላይ የሚወሰድ እርምጃ ነውን? አይደለም። ኃጢአተኛው “እነርሱንም ባይሰማ፣ ለቤተክርስቲያን [ለጉባኤ (አዓት)] ንገራት፤ ደግሞም ቤተ ክርስቲያንን ባይሰማት፣ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ይሁንልህ።”​—ማቴዎስ 18:15-17

      3. ኢየሱስ ንስሐ የማይገባ ኃጢአተኛ ‘እንደ አረመኔና ቀራጭ ይሁንልህ’ ሲል ምን ማለቱ ነበር?

      3 ሐዋርያት አይሁዳውያን ስለሆኑ አንድን ኃጢአተኛ “እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ” አድርጎ መመልከት ምን ማለት እንደሆነ ይገባቸዋል። አይሁዶች አረመኔ ከሆኑት አሕዛብ ጋር ግንኙነት ከማድረግ ይርቁ ነበር፤ የሮም ግብር ሰብሳቢዎች በመሆን ይሠሩ የነበሩትን አይሁዶችም ይጸየፉ ነበር።a (ዮሐንስ 4:9፤ ሥራ 10:28) ስለዚህ ኢየሱስ ጉባኤው አንድን ኃጢአተኛ ካስወጣው ደቀመዛሙርቱ ከእርሱ ጋር መተባበራቸውን ማቆም እንዳለባቸው መምከሩ ነበር። ታዲያ ይህ ኢየሱስ አልፎ አልፎ ከቀራጮች ጋር አብሮ ከመዋሉ ሁኔታ ጋር እንዴት ይስማማል?

  • በዛሬው ጊዜ አምላክን በመሐሪነቱ ምሰሉት
    መጠበቂያ ግንብ—1991 | ሚያዝያ 15
    • a “ቀራጮች በፍልስጥኤም ይኖሩ በነበሩ የአይሁድ ሕዝብ በተለይ ይጠሉ የነበሩት በተለያዩ ምክንያቶች ነበር፦ (1) የእስራኤልን ምድር ለያዘው የውጭ ኃይል ገንዘብ ይሰበስቡ ነበር፤ በዚህም በተዘዋዋሪ ለዚህ ግፍ ድጋፋቸውን ይሰጡ ነበር፤ (2) በደንታ ቢስነታቸው ምክንያት መጥፎ ስም ነበራቸው፤ የገዛ ሕዝባቸው በሆኑ በሌሎች ሰዎች ሐብት የሚበለጽጉ ነበሩ፤ እንዲሁም (3) ሥራቸው ከአሕዛብ ጋር ዘወትር እንዲገናኙ የሚያደርጋቸው ነበር፤ ይህም በሥነ ስርዓት እንዲረክሱ ያደርጋቸዋል። ለቀራጮች ሰዎች የነበራቸው ንቀት በአዲስ ኪዳን ውስጥም ሆነ በራባይ ጽሑፎች ውስጥ ተጽፎ ይገኛል። . . . [በራባይ ጽሑፍ] መሠረት ጥላቻው ለቀራጩ ቤተሰብም የሚተርፍ ነበር።”​—ዘ ኢንተርናሽናል ባይብል ኢንሳይክሎፔዲያ

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ