የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘እርስ በርስ በነፃ ይቅር መባባላችሁን ቀጥሉ’
    መጠበቂያ ግንብ—1997 | ታኅሣሥ 1
    • 1. (ሀ) ጴጥሮስ ሌሎችን “ሰባት ጊዜ” ይቅር እንድንል ሐሳብ ሲያቀርብ ራሱን እንደ ቸር ቆጥሮ ሊሆን የሚችለው ለምንድን ነው? (ለ) ኢየሱስ “እስከ ሰባ ሰባት ጊዜ” ድረስ ይቅር ማለት እንደሚገባን ሲናገር ምን ማለቱ ነበር?

      “ጌታ ሆይ፣ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ልተውለት? እስከ ሰባት ጊዜን?” (ማቴዎስ 18:​21) ጴጥሮስ ይህን ሐሳብ ሲያቀርብ ራሱን በጣም ቸር እንደሆነ አድርጎ አስቦ ሊሆን ይችላል። በወቅቱ የነበረው የረቢዎች ወግ አንድ ሰው ለተመሳሳይ በደል ከሦስት ጊዜ በላይ ይቅርታ ሊያደርግ አይገባም ይል ነበር።a ኢየሱስ “እስከ ሰባ ጊዜ ሰባት [“እስከ ሰባ ሰባት ጊዜ፣” NW] እንጂ እስከ ሰባት ጊዜ አልልህም” ብሎ ሲመልስለት ጴጥሮስ ምን ያህል እንደሚገረም አስቡት! (ማቴዎስ 18:​22) ሰባት ቁጥር ተደጋግሞ መጠቀሱ “በቁጥር ላልተወሰነ ጊዜ” የማለት ያክል ነበር። በኢየሱስ አመለካከት አንድ ክርስቲያን ሌሎችን ይቅር ማለት ያለበት በቁጥር ለተወሰኑ ጊዜያት አይደለም።

  • ‘እርስ በርስ በነፃ ይቅር መባባላችሁን ቀጥሉ’
    መጠበቂያ ግንብ—1997 | ታኅሣሥ 1
    • a የባቢሎናውያን ታልሙድ እንደሚገልጸው ከሆነ አንድ የረቢዎች ወግ እንዲህ ይላል:- “አንድ ሰው ቢበድል በመጀመሪያው፣ በሁለተኛውና በሦስተኛው ጊዜ ይቅር ይባላል፤ በአራተኛው ጊዜ ግን ይቅርታ አይደረግለትም።” (ዮማ 86ቢ) ለዚህ ሐሳብ በከፊል መሠረት የሆነው እንደ አሞጽ 1:​3፤ 2:​6 እንዲሁም ኢዮብ 33:​29 ያሉትን ጥቅሶች በሚመለከት ያላቸው የተሳሳተ ግንዛቤ ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ