የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “በጣም አዘነላቸው”
    “ተከታዬ ሁን”
    • 3 ኢየሱስ ከሕዝቡ ጫጫታ መሃል የለማኞቹን ጩኸት ሰማ። ታዲያ ምን ያደርግ ይሆን? በዚህ ወቅት ብዙ የሚያሳስበውና የሚያስጨንቀው ነገር አለ። ምድራዊ ሕይወቱ የሚጠናቀቅበት የመጨረሻ ሳምንት እየቀረበ ነው። ኢየሩሳሌም ከደረሰ በኋላ እንደሚሠቃይና ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ እንደሚገደል ያውቃል። ያም ሆኖ የለማኞቹን ውትወታ ቸል ብሎ አላለፈም። ቆም አለና እየጮኹ ያሉትን ሰዎች ወደ እሱ እንዲያመጧቸው ጠየቀ። እነሱም “ጌታ ሆይ፣ ዓይናችንን አብራልን” በማለት ለመኑት። ኢየሱስ “በጣም አዘነላቸውና ዓይኖቻቸውን ዳሰሰ”፤ እነሱም ማየት ቻሉ።a ወዲያውኑም ኢየሱስን ይከተሉት ጀመር።​—⁠ሉቃስ 18:​35-43፤ ማቴዎስ 20:​29-34

  • “በጣም አዘነላቸው”
    “ተከታዬ ሁን”
    • a “በጣም አዘነላቸው” ተብሎ የተተረጎመው ግሪክኛ ቃል የመጨረሻውን የርኅራኄ ደረጃ ለመግለጽ ከሚያገለግሉት ግሪክኛ ቃላት አንዱ ነው። አንድ የማመሣከሪያ ጽሑፍ እንደገለጸው ይህ ቃል የሚያመለክተው “የሰውን ሥቃይ አይቶ በስሜት አብሮ መሠቃየትን ብቻ” አይደለም፤ “ሥቃዩን ለማስታገስና ጨርሶ ለማስወገድ ከልብ መጓጓትንም” ያመለክታል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ