የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ንጉሡ ተከታዮቹን በመንፈሳዊ ያጠራቸዋል
    የአምላክ መንግሥት እየገዛ ነው!
    • 1-3. ኢየሱስ ቤተ መቅደሱን የሚያረክስ ነገር እየተከናወነ እንደሆነ ሲመለከት ምን እርምጃ ወሰደ?

      ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ለነበረው ቤተ መቅደስ ታላቅ አክብሮት ነበረው፤ ምክንያቱም ይህ ቤተ መቅደስ ምንን እንደሚወክል ያውቅ ነበር። ቤተ መቅደሱ በምድር ላይ ያለው እውነተኛ አምልኮ ማዕከል ሆኖ ለረጅም ዘመናት አገልግሏል። ይሁንና ቅዱስ አምላክ ለሆነው ለይሖዋ የሚቀርበው አምልኮ ንጹሕና ከርኩሰት የጸዳ መሆን አለበት። ኒሳን 10 ቀን 33 ዓ.ም. ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደሱ በመጣበት ወቅት ግን ቤተ መቅደሱን የሚያረክሱ ነገሮች ሲከናወኑ ተመለከተ፤ በዚህ ወቅት ምን ተሰምቶት ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም። ኢየሱስ የተመለከተው ምን ነበር?—ማቴዎስ 21:12, 13⁠ን አንብብ።

      2 በአሕዛብ አደባባይ የነበሩት ስግብግብ ነጋዴዎችና ገንዘብ መንዛሪዎች፣ ለይሖዋ መሥዋዕት ለማቅረብ የሚመጡትን የአምላክ አገልጋዮች እየበዘበዟቸው ነበር።a ኢየሱስ “በቤተ መቅደሱ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሁሉ አባረረ፤ የገንዘብ መንዛሪዎችን ጠረጴዛዎች . . . ገለባበጠ።” (ከነህምያ 13:7-9 ጋር አወዳድር።) እነዚህ ራስ ወዳድ ሰዎች የአባቱን ቤት “የዘራፊዎች ዋሻ” ስላደረጉት አወገዛቸው። ኢየሱስ ይህን ማድረጉ ለቤተ መቅደሱም ሆነ ቤተ መቅደሱ ለሚወክለው ነገር አክብሮት እንዳለው ያሳያል። ለአባቱ የሚቀርበው አምልኮ ምንጊዜም ንጹሕ መሆን አለበት!

  • ንጉሡ ተከታዮቹን በመንፈሳዊ ያጠራቸዋል
    የአምላክ መንግሥት እየገዛ ነው!
    • a ከሌሎች አገሮች ወደ ቤተ መቅደሱ የሚመጡ አይሁዳውያን የቤተ መቅደሱን ዓመታዊ ግብር የሚከፍሉት በአካባቢው በሚሠራበት ገንዘብ መሆን ነበረበት፤ በመሆኑም ገንዘብ መንዛሪዎች የተወሰነ ዋጋ በማስከፈል ገንዘባቸውን ይቀይሩላቸው ነበር። በተጨማሪም ሰዎቹ መሥዋዕት ለማቅረብ እንስሳት መግዛት ያስፈልጋቸው ይሆናል። ኢየሱስ ነጋዴዎቹን “ዘራፊዎች” በማለት የጠራቸው ለሚሰጡት አገልግሎት በጣም የተጋነነ ዋጋ ይጠይቁ ስለነበር ሳይሆን አይቀርም።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ