-
ይሖዋና ኢየሱስ አንድ እንደሆኑ ሁላችንም አንድ እንሁንመጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018 | ሰኔ
-
-
ፍቅርና ትሕትና በማዳበር ጭፍን ጥላቻን ማሸነፍ
8. በክርስቲያኖች መካከል ላለው አንድነት በጣም አስፈላጊ የሆነው መሠረታዊ እውነታ ምንድን ነው? አብራራ።
8 ኢየሱስ ለአንድነታችን በጣም አስፈላጊ የሆነውን መሠረታዊ እውነታ ለተከታዮቹ ሲናገር “ሁላችሁም ወንድማማቾች ናችሁ” ብሏቸዋል። (ማቴዎስ 23:8, 9ን አንብብ።) “ወንድማማቾች” እንድንባል የሚያደርገን አንዱ ምክንያት ሁላችንም የአዳም ልጆች መሆናችን ነው። (ሥራ 17:26) ምክንያቱ ግን ይህ ብቻ አይደለም። የኢየሱስ ተከታዮች፣ ይሖዋን እንደ ሰማያዊ አባታቸው አድርገው ስለሚቀበሉ ሁሉም ወንድማማችና እህትማማች እንደሆኑ ኢየሱስ ገልጿል። (ማቴ. 12:50) በተጨማሪም የክርስቶስ ተከታዮች በፍቅርና በእምነት የተሳሰረ የአንድ ትልቅ መንፈሳዊ ቤተሰብ አባላት ናቸው። ሐዋርያት በጻፏቸው ደብዳቤዎች ላይ የእምነት ባልንጀሮቻቸውን ‘ወንድሞች’ እና ‘እህቶች’ ብለው የጠሯቸው ለዚህ ነው።—ሮም 1:13፤ 1 ጴጥ. 2:17፤ 1 ዮሐ. 3:13a
-