-
የምንኖረው በመጨረሻው ቀን ነው!ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት
-
-
2. የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ምን ጥያቄ አቅርበውለት ነበር? ምንስ ብሎ መለሰላቸው?
2 ለምሳሌ ያህል ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ አንስተዋቸው ለነበሩት አንዳንድ ጥያቄዎች የሰጣቸውን መልሶች እንመልከት። ኢየሱስ ከመሞቱ ከሦስት ቀናት በፊት “የመገኘትህና የነገሮች ሥርዓት መደምደሚያ ምልክት ምን ይሆናል?” ብለው ጠየቁት።a (ማቴዎስ 24:3 አዓት) ኢየሱስም ሲመልስላቸው ይህ ለአምላክ ደንታ የሌለው ዓለም ወደ መጨረሻው ቀን የገባ መሆኑን በግልጽ የሚያመለክቱ ሁኔታዎችንና ክንውኖችን ነገራቸው።
-
-
የምንኖረው በመጨረሻው ቀን ነው!ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት
-
-
a አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች “የነገሮች ሥርዓት” ከማለት ይልቅ “ዓለም” ይላሉ። በደብልዩ ኢ ቫይን የተዘጋጀው ኤክስፖዚተሪ ዲክሽነሪ ኦቭ ኒው ቴስተመንት ወርድስ የተባለ መዝገበ ቃላት “አይኦን” የሚለው የግሪክኛ ቃል “ከ—እስከ ተብሎ ያልተወሰነ ዘመን ወይም በዘመኑ ውስጥ ከሚከናወኑት ነገሮች አንፃር የሚታይ ጊዜ ማለት ነው” ይላል። የፓርክረስት ግሪክ ኤንድ ኢንግሊሽ ሌክሲከን ቱ ዘ ኒው ቴስተመንት (ገጽ 17) በዕብራውያን 1:2 ላይ የተጠቀሰውን አይኦነስ (የብዙ ቁጥር) ሲያብራራ ከሰጣቸው ፍቺዎች አንዱ “ይህ የነገሮች ሥርዓት” የሚል ነው። ስለዚህ “የነገሮች ሥርዓት” የሚለው አተረጓጎም ከጥንቱ የግሪክኛ ጽሑፍ ጋር የሚስማማ ነው።
-