-
ከታላንቱ ምሳሌ ትምህርት ማግኘትመጠበቂያ ግንብ—2015 | መጋቢት 15
-
-
4, 5. ሰውየው ወይም ጌታው ማንን ያመለክታል? አንድ ታላንት ምን ያህል ዋጋ ነበረው?
4 ማቴዎስ 25:14-30ን አንብብ። ቀደም ካሉት ዓመታት ጀምሮ ጽሑፎቻችን በምሳሌው ላይ የተገለጸው ሰው ወይም ጌታው ኢየሱስ እንደሆነና ወደ ሌላ አገር የተጓዘው ደግሞ በ33 ዓ.ም. ወደ ሰማይ ሲያርግ እንደሆነ ገልጸዋል። ኢየሱስ፣ ከዚያ ቀደም በተናገረው ምሳሌ ላይ ወደ ሌላ አገር የሚሄድበት ዓላማ “ንጉሣዊ ሥልጣኑን [ለመረከብ]” እንደሆነ ጠቁሟል። (ሉቃስ 19:12) ኢየሱስ በመንግሥቱ ላይ ሙሉ ሥልጣን ያገኘው ልክ ወደ ሰማይ እንደተመለሰ አልነበረም።b ከዚህ ይልቅ ‘በአምላክ ቀኝ ተቀምጦ ጠላቶቹ ለእግሩ እንደ መርገጫ እስኪደረጉ ድረስ ይጠባበቅ ነበር።’—ዕብ. 10:12, 13
-
-
ከታላንቱ ምሳሌ ትምህርት ማግኘትመጠበቂያ ግንብ—2015 | መጋቢት 15
-
-
d ሐዋርያት ከሞቱ በኋላ ሰይጣን ያስነሳው ክህደት ለበርካታ ዘመናት ተስፋፍቶ ቆይቷል። በዚያ ወቅት፣ እውነተኛ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርትን እንዲያፈሩ ለክርስቲያኖች የተሰጠውን ተልእኮ በቀጣይነት የሚያከናውን አልነበረም። ይሁንና ‘በመከሩ ወቅት’ ይኸውም በመጨረሻዎቹ ቀናት ይህ ሁኔታ ተለወጠ። (ማቴ. 13:24-30, 36-43) የሐምሌ 15, 2013 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 9-12 ተመልከት።
-
-
ከታላንቱ ምሳሌ ትምህርት ማግኘትመጠበቂያ ግንብ—2015 | መጋቢት 15
-
-
8. እያንዳንዱ ባሪያ የተሰጠው ታላንት መጠን ቢለያይም ጌታው ከእነሱ ምን ይጠብቅ ነበር?
8 በታላንቱ ምሳሌ ላይ ጌታው ለአንዱ ባሪያ አምስት ታላንት፣ ለሌላው ሁለት፣ ለሌላው ደግሞ አንድ ብቻ እንደሰጠ ተገልጿል። (ማቴ. 25:15) እያንዳንዱ ባሪያ የተሰጠው ታላንት መጠን ቢለያይም ሁሉም ባሪያዎች የተሰጣቸውን ታላንት በመጠቀም ረገድ ትጋት እንዲያሳዩ ይኸውም በአገልግሎቱ አቅማቸው የሚፈቅደውን ያህል እንዲካፈሉ ጌታው ይጠብቅባቸዋል። (ማቴ. 22:37፤ ቆላ. 3:23) በመጀመሪያው መቶ ዘመን፣ በ33 ዓ.ም. ከዋለው የጴንጤቆስጤ በዓል አንስቶ የክርስቶስ ተከታዮች በታላንቱ መነገድ ጀመሩ። በስብከቱና ደቀ መዛሙርት በማድረጉ ሥራ ያሳዩት ትጋት በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ላይ በሚገባ ተመዝግቦ ይገኛል።d—ሥራ 6:7፤ 12:24፤ 19:20
በፍጻሜው ዘመን በታላንቱ መነገድ
9. (ሀ) ሁለቱ ታማኝ ባሪያዎች በታላንታቸው ምን አደረጉ? ይህስ ምን ያሳያል? (ለ) “ሌሎች በጎች” ምን ሚና ይጫወታሉ?
9 በፍጻሜው ዘመን በተለይም ከ1919 ወዲህ ባለው ጊዜ፣ በምድር ላይ ያሉት የክርስቶስ ታማኝ ቅቡዓን ባሪያዎች በጌታው ታላንት ሲነግዱ ቆይተዋል። እንደ ሁለቱ ባሪያዎች ሁሉ ቅቡዓን ወንድሞችና እህቶችም በተሰጣቸው ንብረት አቅማቸው የሚፈቅደውን ያህል ሠርተዋል። ማን አምስት ታላንት፣ ማን ሁለት ታላንት እንደተሰጠው መገመት አያስፈልግም። በምሳሌው ላይ ሁለቱም ባሪያዎች ጌታው የሰጣቸውን ንብረት እጥፍ እንዳደረጉ ተገልጿል፤ ስለዚህ ሁለቱም በእኩል ደረጃ ትጋት አሳይተዋል። ምድራዊ ተስፋ ያላቸው ክርስቲያኖች በዚህ ሥራ ላይ ምን ሚና ይጫወታሉ? ትልቅ ሚና አላቸው። ኢየሱስ ስለ በጎቹና ፍየሎቹ የተናገረው ምሳሌ እንደሚያሳየው ምድራዊ ተስፋ ያላቸው ክርስቲያኖች በስብከቱና በማስተማሩ ሥራ የኢየሱስን ቅቡዓን ወንድሞች በታማኝነት የመደገፍ መብት አላቸው። በእነዚህ የመጨረሻዎቹ ቀናት ሁለቱ ቡድኖች፣ ደቀ መዛሙርት በማድረጉ ሥራ እንደ “አንድ መንጋ” ሆነው በቅንዓት እየሠሩ ነው።—ዮሐ. 10:16
10. ኢየሱስ መገኘቱን የሚያሳየው ምልክት አንዱ ጉልህ ገጽታ ምንድን ነው?
10 ጌታው ውጤት መጠበቁ የተገባ ነው። ቀደም ሲል እንደተገለጸው በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩ ታማኝ ደቀ መዛሙርቱ ንብረቱ እንዲበዛ አድርገዋል። የታላንቱ ምሳሌ በሚፈጸምበት በዚህ የመጨረሻ ዘመን ስላለው ሁኔታስ ምን ማለት ይቻላል? ታማኝና ታታሪ የሆኑት የኢየሱስ አገልጋዮች በታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የስብከቱንና ደቀ መዛሙርት የማድረጉን ሥራ አከናውነዋል። የኢየሱስ ተከታዮች በኅብረት የሚያካሂዱት ሥራ በየዓመቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ የመንግሥቱ አስፋፊዎች እንዲጨመሩ አድርጓል፤ በዚህም ምክንያት የስብከቱና የማስተማሩ ሥራ፣ ኢየሱስ በመንግሥቱ ሥልጣን መገኘቱን የሚያሳየው ምልክት አንዱ ጉልህ ገጽታ መሆን ችሏል። በእርግጥም ጌታቸው እንደሚደሰት ጥርጥር የለውም!
ክርስቶስ ውድ የሆነውን የስብከት ሥራ ለአገልጋዮቹ በአደራ ሰጥቷል (አንቀጽ 10ን ተመልከት)
-