-
የበጎቹና የፍየሎቹ የወደፊት ዕጣ ምንድን ነው?መጠበቂያ ግንብ—1995 | ጥቅምት 15
-
-
የእያንዳንዱ ቡድን የወደፊት ዕጣ ምንድን ነው?
16, 17. የበጎቹ የወደፊት ዕጣ ምንድን ነው?
16 ኢየሱስ ለበጎቹ ሲፈርድላቸው “እናንተ የአባቴ ብሩካን፣ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት [“ከተመሠረተበት” አዓት] ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ” ብሏቸዋል። “ኑ” የሚለው ግብዣ እንዴት ያለ ሞቅ ያለ ግብዣ ነው! የሚመጡት ወዴት ነው? ወደ ዘላላም ሕይወት ነው። ይህም “ጻድቃን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ” በሚለው የማጠቃለያ ሐሳቡ ላይ ተገልጿል።—ማቴዎስ 25:34, 46
17 ኢየሱስ በመክሊቶቹ ምሳሌ ላይ ከእሱ ጋር በሰማይ የሚገዙት ሰዎች ምን እንደሚፈለግባቸው አሳይቷል፤ ሆኖም በዚህ ምሳሌ ላይ የገለጸው የመንግሥቱ ዜጎች ምን ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው። (ማቴዎስ 25:14–23) በጎቹ ለኢየሱስ ወንድሞች የሙሉ ልብ ድጋፍ በመስጠታቸው ምክንያት የመንግሥቱን ምድራዊ ግዛት ይወርሳሉ። አምላክ ሊቤዡ ለሚችሉ ሰዎች “ዓለም ከተመሠረተበት” ጊዜ ጀምሮ ያዘጋጀላቸውን በገነት ምድር ውስጥ የመኖር ተስፋ ያገኛሉ።—ሉቃስ 11:50, 51
-
-
የበጎቹና የፍየሎቹ የወደፊት ዕጣ ምንድን ነው?መጠበቂያ ግንብ—1995 | ጥቅምት 15
-
-
19 የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ይህ አነጋገር ፍየል መሰል የሆኑት ሰዎች የማይሞቱ ነፍሳት በመሆን በዘላለም እሳት ይሠቃያሉ ማለት እንዳልሆነ ያውቃሉ። ይህ በፍጹም ሊሆን አይችልም፤ ምክንያቱም ሰዎች ነፍሳት ናቸው እንጂ በውስጣቸው የማይሞቱ ነፍሳት የላቸውም ። (ዘፍጥረት 2:7 አዓት ፤ መክብብ 9:5, 10፤ ሕዝቅኤል 18:4) ዳኛው በፍየሎቹ ላይ “የዘላለም እሳት” በመበየኑ ወደፊት የመኖር ተስፋ የሌለው ጥፋት ይደርስባቸዋል። ይህ ፍርድ ለሰይጣንና ለአጋንንቱ ጭምር ዘላለማዊ ጥፋት ያስከትልባቸዋል። (ራእይ 20:10, 14) ስለዚህ ይሖዋ የሾመው ዳኛ ሁለት ተቃራኒ ፍርዶችን ይሰጣል። በጎቹን “ኑ” የሚላቸው ሲሆን ፍየሎቹን ደግሞ “ከእኔ ሂዱ” ይላቸዋል። በጎቹ “የዘላለም ሕይወት” ያገኛሉ። ፍየሎቹ “የዘላለም ቅጣት” ይቀበላሉ።—ማቴዎስ 25:46b
-
-
የበጎቹና የፍየሎቹ የወደፊት ዕጣ ምንድን ነው?መጠበቂያ ግንብ—1995 | ጥቅምት 15
-
-
21 ታዲያ ስለ በጎቹና ፍየሎቹ ምሳሌ ያገኘነው ይህ ተጨማሪ ማስተዋል ለእኛ ምን ትርጉም ይኖረዋል? በአሁኑ ጊዜ ሰዎች ሚናቸውን እየለዩ ነው። አንዳንዶች ‘ወደ ጥፋት በሚወስደው ሰፊ መንገድ’ ላይ ሲሆኑ ሌሎች ‘ወደ ሕይወት በሚወስደው ጠባብ መንገድ’ ላይ ለመቆየት እየጣሩ ነው። (ማቴዎስ 7:13, 14) ይሁን እንጂ ኢየሱስ በበጎቹና በፍየሎቹ ላይ የመጨረሻውን ፍርድ የሚሰጥበት በምሳሌው ውስጥ የተገለጸው ጊዜ ገና ወደፊት ይጠብቀናል። የሰው ልጅ የዳኝነት ተግባሩን ለማከናወን ሲመጣ ብዙ እውነተኛ ክርስቲያኖች የሆኑ ራሳቸውን የወሰኑ “እጅግ ብዙ ሰዎች” ‘የታላቁ መከራን’ የመጨረሻ ክፍል አልፈው ወደ አዲሱ ዓለም ለመግባት ብቁ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ፍርድ ይሰጣል። ይህ ተስፋ በአሁኑ ጊዜ ሊያስደስታቸው ይገባል። (ራእይ 7:9, 14) በሌላ በኩል ከ“አሕዛብ ሁሉ” መካከል በጣም ብዙ ሰዎች እንደ ልበ ደንዳና ፍየሎች ሆነዋል። እነዚህ ሰዎች “ወደ ዘላለም ቅጣት . . . ይሄዳሉ።” ይህ ለምድር እንዴት ያለ እፎይታ ያመጣል!
-
-
የበጎቹና የፍየሎቹ የወደፊት ዕጣ ምንድን ነው?መጠበቂያ ግንብ—1995 | ጥቅምት 15
-
-
b ኤል ኢቫንሄሊዮ ደ ማቴኦ የተባለ መጽሐፍ እንዲህ በማለት ይገልጻል፦ “የዘላለም ሕይወት ፍጻሜ የሌለው ሕይወት ነው፤ ከማያዳግም ቅጣት ጋር የሚቃረን ነገር ነው። አይኦንየስ የተባለው ግሪክኛ ቅጽል በአንደኛ ደረጃ የሚያመለክተው ጊዜን ሳይሆን የአንድን ነገር ባሕርይ ነው። ይህ የማያዳግም ጥፋት ዘላለማዊ ሞት ነው።”—ጡረታ የወጡት፣ ፕሮፌሰር ጅዋን ማቲዮስ (መጽሐፍ ቅዱሳዊ ተቋም፣ ሮም) እና ፕሮፌሰር ፌርናንዶ ካማቾ፣ (መንፈሳዊ ተቋም፣ ሲቬሌ) ማድሪድ፣ ስፔይን 1981
-