የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w99 8/15 ገጽ 32
  • “ጨው ጣዕሙን ካጣ”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ጨው ጣዕሙን ካጣ”
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
w99 8/15 ገጽ 32

“ጨው ጣዕሙን ካጣ”

ለእርሱ ሲባል ጦርነቶች ተካሂደዋል። እንደ ገንዘብ ሆኖ አገልግሏል። በጥንቷ ቻይና በዋጋ ረገድ ከወርቅ ቀጥሎ ሁለተኛ ደረጃ ነበረው። አዎን፣ የሰው ልጅ ከጥንት ጀምሮ ጨውን ከፍተኛ ዋጋ እንዳለው ዕቃ አድርጎ ሲመለከተው ቆይቷል። ዛሬም ቢሆን ጨው ቁስል የመሻርና ፀረ ሕዋሳት ባሕርይ እንዳለው ይነገርለታል። እንዲሁም በምድር ዙሪያ ምግብ ለማጣፈጥና አንዳንድ ዕቃዎችን ሳይበላሹ ለማቆየት ያገለግላል።

ጨው ካሉት ተፈላጊ ባሕርያትና ጥቅሞች አንጻር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በምሳሌያዊ መንገድ መጠቀሱ ምንም አያስደንቅም። ለምሳሌ ያህል የሙሴ ሕግ በመሠዊያው ላይ ለይሖዋ የሚቀርብ ማንኛውም መሥዋዕት በጨው መጣፈጥ እንዳለበት ያዛል። (ዘሌዋውያን 2:​13) እንዲህ ይደረግ የነበረው መሥዋዕት ለቀረቡት ነገሮች ጣዕም ለመጨመር ተብሎ ሳይሆን ጨው ከብክለት ወይም ከብልሽት ነፃ መሆንን ስለሚያመለክት ሊሆን ይችላል።

ኢየሱስ ክርስቶስ በዝነኛ የተራራ ስብከቱ ላይ ተከታዮቹን “እናንተ የምድር ጨው ናችሁ” ብሏቸዋል። (ማቴዎስ 5:​13 የ1980 ትርጉም) ኢየሱስ ይህን ሲል ለሌሎች ሰዎች የሚያዳርሱት ስለ አምላክ መንግሥት የሚገልጸው ስብከት የሚሰሙትን ሰዎች ጠብቆ እንደሚያቆይ በሌላ አባባል ሕይወት ሰጪ እንደሚሆንላቸው ማመልከቱ ነበር። በእርግጥም የኢየሱስን ቃል በተግባር የሚያውሉ ሰዎች የሚኖሩበትና የሚያገለግሉበት ኅብረተሰብ ካለው ሥነ ምግባራዊም ሆነ መንፈሳዊ ብልሽት ይጠበቃሉ።​—⁠1 ጴጥሮስ 4:​1-3

ሆኖም ኢየሱስ በመቀጠል የሚከተለውን ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል:- “ነገር ግን ጨው ጣዕሙን ካጣ . . . ወደ ውጪ ከመጣልና በሰው እግር ከመረገጥ በቀር ከእንግዲህ ወዲያ ለምንም አይጠቅምም።” የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁር የሆኑት አልበርት ባርነስ በዚህ ላይ ሐሳብ ሲሰጡ በኢየሱስና በደቀ መዛሙርቱ ዘመን የሚታወቀው ጨው “ያልተጣራ፣ ከዕፅዋት ቅሪትና ከአፈር ጋር የተቀላቀለ” እንደነበር ተናግረዋል። ስለዚህ ጨዉ የጨውነት ባሕርይውን ካጣ “የቀረው አብዛኛው ነገር የምድር ንጥረ ነገር” ሊሆን ይችላል። ባርነስ “ይህ ንጥረ ነገር ደግሞ መንገድ ለማልበስ የሚያገለግል ጠጠር ከመሆን በቀር . . . ሌላ ፋይዳ አልነበረውም” ብለዋል።

ክርስቲያኖች ይህን ማስጠንቀቂያ በመከተል ለሕዝብ የሚሰጡትን ምስክርነት ላለማቆም ወይም አምላካዊ ወዳልሆኑ ልማዶች ላለመመለስ መጠንቀቅ አለባቸው። ይህ ካልሆነ ግን መንፈሳዊ አቋማቸው ሊያሽቆለቁልና ‘ጣዕሙን እንዳጣ ጨው’ ፋይዳ ቢስ ሊሆኑ ይችላሉ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ