የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘ከሰማይ የሆነውን ጥበብ’ በአኗኗርህ እያንጸባረቅህ ነው?
    ወደ ይሖዋ ቅረብ
    • 11 የእምነት ባልንጀራህን እንዳስቀየምክ ከተሰማህ ምን ማድረግ ይኖርብሃል? ኢየሱስ እንዲህ ሲል ተናግሯል፦ “እንግዲያው መባህን ወደ መሠዊያው ባመጣህ ጊዜ ወንድምህ በአንተ ቅር የተሰኘበት ነገር እንዳለ ትዝ ካለህ መባህን በመሠዊያው ፊት ትተህ ሂድ። በመጀመሪያ ከወንድምህ ጋር ታረቅ፤ ከዚያም ተመልሰህ መባህን አቅርብ።” (ማቴዎስ 5:23, 24) ቀዳሚውን እርምጃ ወስደህ ወንድምህን በማነጋገር ይህን ምክር ልትሠራበት ትችላለህ። ይህን የምታደርግበት ዓላማ ምንድን ነው? ‘ከወንድምህ ጋር መታረቅ’ ነው።b ይህ እንዲሆን ደግሞ ቅር የሚያሰኘው ምንም ምክንያት እንደሌለው ከመግለጽ ይልቅ ስሜቱን እንደጎዳኸው አምነህ መቀበል ይኖርብሃል። ቀደም ሲል የነበራችሁን ሰላማዊ ግንኙነት የማደስ ግብ ይዘህ ካነጋገርከውና በውይይታችሁ ወቅትም ይህንን አመለካከት ካንጸባረቅህ በመካከላችሁ የነበረው አለመግባባት ተወግዶ ይቅር ልትባባሉ ትችላላችሁ። ቀዳሚውን እርምጃ በመውሰድ ከወንድምህ ጋር እርቅ ለመፍጠር መጣርህ በአምላክ ጥበብ እንደምትመራ ያሳያል።

  • ‘ከሰማይ የሆነውን ጥበብ’ በአኗኗርህ እያንጸባረቅህ ነው?
    ወደ ይሖዋ ቅረብ
    • b “ታረቅ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ አገላለጽ “ጠላትነትን አስወግዶ ወዳጅነት መመሥረት፣ እርቅ መፍጠር፣ ቀድሞ ወደነበረው ጥሩ ግንኙነት ወይም ስምምነት መመለስ” የሚል ትርጉም ያስተላልፋል። በመሆኑም ዓላማህ ከተቻለ፣ ቅር በተሰኘው ግለሰብ ልብ ውስጥ የተፈጠረውን መጥፎ ስሜት በማስወገድ ለውጥ ማምጣት ነው።—ሮም 12:18

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ