የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ከአምላክ ጋር ትሄዳለህ?
    መጠበቂያ ግንብ—2005 | ኅዳር 1
    • 5. ኢየሱስ በዕድሜ ላይ አንድ ክንድ ስለመጨመር የተናገረው ለምንድን ነው?

      5 መጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ቦታዎች ላይ ሕይወትን ከጉዞ ወይም ከመሄድ ጋር ያመሳስለዋል። ንጽጽሩ አንዳንድ ጊዜ በቀጥታ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ በተዘዋዋሪ መንገድ ተገልጿል። ለምሳሌ ያህል ኢየሱስ “ለመሆኑ ከእናንተ መካከል ተጨንቆ በዕድሜው ላይ አንዲት ሰዓት [“ክንድ፣” NW] መጨመር የሚችል አለን?” ብሎ ነበር። (ማቴዎስ 6:27) እዚህ ላይ የተጠቀሱት አንዳንድ ቃላት በአእምሮህ ውስጥ ጥያቄ ይፈጥሩብህ ይሆናል። ኢየሱስ በዕድሜ ላይ ስለመጨመር ሲናገር የጊዜ ሳይሆን የርዝመት መለኪያ የሆነውን ‘አንድ ክንድ’ የተጠቀመው ለምንድን ነው?a ኢየሱስ ሕይወትን ከጉዞ ጋር እንዳዛመደው በግልጽ ማየት ይቻላል። መጨነቅ በሕይወት ጉዞህ ላይ ጥቂት እርምጃ እንኳን እንድትጨምር ሊያደርግህ እንደማይችል ትምህርት እየሰጠ ነበር። ይሁን እንጂ ከአምላክ ጋር በምናደርገው ጉዞ በርቀቱ ላይ የምናመጣው ለውጥ እንደሌለ ሊሰማን ይገባናል? በጭራሽ! ይህ ‘ከአምላክ ጋር መሄድ የሚያስፈልገን ለምንድን ነው?’ ወደሚለው ሁለተኛ ጥያቄያችን ይወስደናል።

  • ከአምላክ ጋር ትሄዳለህ?
    መጠበቂያ ግንብ—2005 | ኅዳር 1
    • a አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች በዚህ ጥቅስ ላይ ያለውን “ክንድ” የሚለውን ቃል “ጥቂት ጊዜ” (ዚ ኢምፋቲክ ዲያግሎት) ወይም “አንድ ደቂቃ” (ኤ ትራንስሌሽን ኢን ዘ ላንግዊጅ ኦቭ ዘ ፒፕል፣ በቻርልስ ቢ ዊልያምስ) እንደሚሉት ባሉ የጊዜ መለኪያዎች ተክተውታል። ሆኖም መጀመሪያ በተጻፈበት ቋንቋ የገባው ቃል ቀጥተኛ ትርጉሙ ክንድ የሚል ሲሆን ርዝመቱም ወደ 45 ሴንቲ ሜትር ገደማ ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ