የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “የራስ ጠጒራችሁ እንኳ አንድ ሳይቀር” በይሖዋ ተቆጥሯል
    መጠበቂያ ግንብ—2005 | ነሐሴ 1
    • 6 ኢየሱስ ሐዋርያቱ ለምን መፍራት እንደሌለባቸው ለማስረዳት ሁለት ምሳሌዎችን ተጠቀመ። እንዲህ አላቸው:- “በአንድ ሳንቲም ከሚሸጡት ሁለት ድንቢጦች አንዲቷ እንኳ ያለ አባታችሁ ፈቃድ ምድር ላይ አትወድቅም። የራስ ጠጒራችሁ እንኳ አንድ ሳይቀር የተቈጠረ ነው። ስለዚህ አትፍሩ፤ ከብዙ ድንቢጦች ይልቅ ዋጋችሁ የከበረ ነው።” (ማቴዎስ 10:29-31) ኢየሱስ እዚህ ላይ መከራ በሚያጋጥመን ጊዜ አለመፍራትን፣ በግለሰብ ደረጃ ይሖዋ ያስብልኛል ብሎ ከመተማመን ጋር አያይዞ እንደገለጸው አስተውል። ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ያለ እምነት እንደነበረው ከሁኔታው መረዳት ይቻላል። እንዲህ ብሎ ጽፏል:- “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ፣ ማን ሊቃወመን ይችላል? ለገዛ ልጁ ያልሳሳለት፣ ነገር ግን ለሁላችንም አሳልፎ የሰጠው እርሱ፣ ሁሉንስ ነገር ከእርሱ ጋር እንደ ምን በልግስና አይሰጠን?” (ሮሜ 8:31, 32) አንተም ለይሖዋ ታማኝ እስከሆንክ ድረስ ምንም ዓይነት ችግር ቢያጋጥምህ እርሱ በግለሰብ ደረጃ እንደሚያስብልህ እርግጠኛ መሆን ትችላለህ። ኢየሱስ ለሐዋርያቱ የሰጣቸውን ማሳሰቢያ በጥልቅ እየመረመርን ስንሄድ ይሖዋ በግለሰብ ደረጃ እንደሚያስብልህ በግልጽ መረዳት ትችላለህ።

      የአንዲት ድንቢጥ ዋጋ

      7, 8. (ሀ) በኢየሱስ ዘመን ድንቢጦች እንዴት ይታዩ ነበር? (ለ) ኢየሱስ በማቴዎስ 10:29 ላይ ትንንሽ ድንቢጦችን የሚያመለክት ግሪክኛ ቃል የተጠቀመው ለምን ሊሆን ይችላል?

      7 ኢየሱስ የተናገራቸው ምሳሌዎች ይሖዋ ለእያንዳንዱ አገልጋዩ እንደሚያስብ በሚገባ ያስገነዝባሉ። እስቲ መጀመሪያ ስለ ድንቢጦች እንመልከት። በኢየሱስ ዘመን ድንቢጦች ለምግብነት ይውሉ ነበር፤ ይሁን እንጂ ሰብል ያጠፉ ስለነበር በአብዛኛው እንደ ተባይ ተደርገው ይታዩ ነበር። ድንቢጦች በብዛት የሚገኙና ርካሽ የነበሩ በመሆኑ በአሁኑ ገንዘብ መሠረት ሁለቱን ከአምስት ሳንቲም ባነሰ ዋጋ መግዛት ይቻል ነበር። የዚህ እጥፍ ከተከፈለ ደግሞ አራት ብቻ ሳይሆን አምስት ድንቢጦች መግዛት ይቻላል። አንደኛዋ ወፍ እንዲያው ምንም ዋጋ የሌላት ይመስል ምራቂ ተደርጋ ትሰጣለች!—ሉቃስ 12:6

      8 የዚህችን ወፍ መጠንም ተመልከት። ለአካለ መጠን የደረሰች ድንቢጥ እንኳን ከሌሎች የወፍ ዝርያዎች ጋር ስትወዳደር በጣም ትንሽ ነች። እንዲህም ሆኖ በማቴዎስ 10:29 ላይ “ድንቢጦች” ተብሎ የተተረጎመው ግሪክኛ ቃል በቀጥታ የሚናገረው ስለ ትንንሽ ድንቢጦች ነው። ኢየሱስ ሐዋርያቱ ከቁም ነገር የማትቆጠር አንዲት ትንሽ ወፍ ወደ አእምሯቸው እንዲያመጡ ፈልጎ እንደነበረ ከሁኔታው መረዳት ይቻላል።

      9. ኢየሱስ የጠቀሰው የድንቢጦቹ ምሳሌ ምን ቁም ነገር ይዟል?

      9 ኢየሱስ ስለ ድንቢጦች የተናገረው ምሳሌ ትልቅ ቁም ነገር ይዟል፤ ይኸውም በሰዎች ዘንድ ምንም ዋጋ እንደሌለው ተደርጎ የሚታየውን ነገር ይሖዋ አምላክ ትልቅ ቦታ ይሰጠዋል። ኢየሱስ የዚህን ጉዳይ እውነትነት ይበልጥ ለማጉላት ሲል ትንሿ ድንቢጥ ያለ ይሖዋ ፈቃድ “ምድር ላይ አትወድቅም” በማለት ጨምሮ ተናግሯል።c ትምህርቱ ግልጽ ነው። ይሖዋ አምላክ በጣም ትንሽ ለሆነችና ማንም ከቁም ነገር ለማይቆጥራት ወፍ ትኩረት ከሰጠ እርሱን ማገልገል የሚፈልግ ሰው ስለሚገጥመው ሁኔታ ምን ያህል ያስብ!

  • “የራስ ጠጒራችሁ እንኳ አንድ ሳይቀር” በይሖዋ ተቆጥሯል
    መጠበቂያ ግንብ—2005 | ነሐሴ 1
    • c አንዳንድ ምሁራን የድንቢጧ መውደቅ መሞቷን ብቻ የሚያመለክት ላይሆን እንደሚችል አስተያየት ይሰጣሉ። ጥቅሱ በመጀመሪያ በተጻፈበት ግሪክኛ ቋንቋ የተጠቀሰው ቃል ወፏ ምግብ ለመለቃቀም መሬት ላይ ማረፏን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል ይላሉ። ይህ አባባላቸው እውነት ከሆነ አምላክ የወፏን መሞት ብቻ ሳይሆን ለምታደርገው ዕለታዊ እንቅስቃሴ ትኩረት ይሰጣል እንዲሁም ያስብላታል ማለት ነው።—ማቴዎስ 6:26

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ