የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋ—የእውነተኛ ፍትሕና ጽድቅ ምንጭ
    መጠበቂያ ግንብ—1998 | ነሐሴ 1
    • 11. (ሀ) ፈሪሳውያን ኢየሱስን በሰንበት ቀን ስለ መፈወስ የጠየቁት ለምን ነበር? (ለ) የኢየሱስ መልስ ምን የሚያሳይ ነበር?

      11 ኢየሱስ በ31 እዘአ የፀደይ ወራት በገሊላ በማገልገል ላይ እንዳለ በአንድ ምኩራብ ውስጥ እጁ የሰለለች ሰው ይመለከታል። ቀኑ ሰንበት ስለነበረ ፈሪሳውያን ኢየሱስን “በሰንበት መፈወስ ተፈቅዶአልን?” ብለው ጠየቁት። ለዚህ ምስኪን ሰው ስቃይ እውነተኛ አሳቢነት ከማሳየት ይልቅ ኢየሱስን የሚወነጅሉበት ነገር ለማግኘት ይፈልጉ እንደነበር ከጥያቄያቸው መገንዘብ ይቻላል። ኢየሱስ ጨካኝ በሆነው ልባቸው ማዘኑ ምንም አያስገርምም! ከዚያም ኢየሱስ “በሰንበት በጎ ማድረግ ተፈቅዶአልን?” በማለት ጥያቄያቸውን በጥያቄ መለሰላቸው። ዝም ባሉት ጊዜ ኢየሱስ በሰንበት ቀን ወደ ጉድጓድ የገባን በግ ያወጡ ወይም አያወጡ እንደሆነ በመጠየቅ የራሱን ጥያቄ መለሰ።b ኢየሱስ “እንግዲህ ሰው ከበግ ይልቅ እንደምን አይበልጥም!” በማለት ማንም ሊክደው የማይችል ሐቅ ተናገረ። “ስለዚህ በሰንበት መልካም መሥራት ተፈቅዶአል [ወይም፣ ትክክል ነው]” በማለት ደመደመ። የአምላክ ፍትሕ በሰብዓዊ ወጎች ማነቆ ውስጥ መግባት የለበትም። ኢየሱስ ይህን ነጥብ ግልጽ ካደረገ በኋላ የሰውየውን እጅ ፈወሰለት።​—⁠ማቴዎስ 12:​9-13፤ ማርቆስ 3:​1-5

  • ይሖዋ—የእውነተኛ ፍትሕና ጽድቅ ምንጭ
    መጠበቂያ ግንብ—1998 | ነሐሴ 1
    • b የኢየሱስ ምሳሌ በጣም ተስማሚ ነበር፤ ምክንያቱም የአይሁዳውያኑ የቃል ሕግ በሰንበት ቀን ችግር ለገጠመው እንስሳ እርዳታ ማድረግን ይፈቅድ ነበር። በሌሎች ጊዜያትም በዚሁ ጉዳይ ላይ ማለትም በሰንበት ቀን መፈወስ ሕጋዊ ነው ወይስ አይደለም በሚለው ጉዳይ ላይ አለመግባባቶች ተከስተው ነበር።​—⁠ሉቃስ 13:​10-17፤ 14:​1-6፤ ዮሐንስ 9:​13-16

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ