የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋ በሙሉ ነፍስ የምታቀርቡትን አገልግሎት ከፍ አድርጎ ይመለከተዋል
    መጠበቂያ ግንብ—1997 | ጥቅምት 15
    • 16. (ሀ) ኢየሱስ አንዲት ድሃ መበለት ያኖረችውን መዋጮ ሊያስተውል የቻለው እንዴት ነው? (ለ) የመበለቲቱ ሳንቲሞች ዋጋቸው ምን ያህል ነበር?

      16 ከጥቂት ቀናት በኋላ ማለትም በኒሳን 11፣ ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ብዙ ሰዓታት አሳለፈ፤ በዚሁ ጊዜም በምን ሥልጣን ነገሮችን እንደሚያደርግ እንዲሁም ቀረጥን፣ ትንሣኤንና ሌሎች ጉዳዮችን በሚመለከት ለቀረቡለት አስቸጋሪና ድንገተኛ ጥያቄዎች መልስ ሲሰጥ ቆየ። ጻፎችንና ፈሪሳውያንንም ከሚያደርጓቸው ሌሎች ነገሮች በተጨማሪ ‘የመበለቶችን ቤት ስለሚበሉ’ አወገዛቸው። (ማርቆስ 12:​40) ከዚያም ኢየሱስ ከሁኔታዎች ለመረዳት እንደሚቻለው ወደ ሴቶች ሸንጎ ገብቶ አረፍ አለ፤ በዚህ ቦታ በአይሁዳውያን ወግ መሠረት 13 የገንዘብ ማስቀመጫ ዕቃዎች ተቀምጠው ነበር። ኢየሱስ ለጥቂት ጊዜ ተቀምጦ ሰዎች መዋጮአቸውን ሲያኖሩ በጥንቃቄ ይመለከት ነበር። ብዙ ሃብታሞች መዋጮ ለማድረግ የመጡ ሲሆን ምናልባትም የአንዳንዶቹ ሁኔታ ራስን የማመጻደቅ አልፎ ተርፎም የይታይልኝ ዓይነት መንፈስ የሚያንጸባርቅ ሳይሆን አይቀርም። (ከማቴዎስ 6:​2 ጋር አወዳድር።) የኢየሱስ ትኩረት አንዲት ሴት ላይ አረፈ። ሌላ ሰው ቢሆን ስለ እርሷም ሆነ ስላኖረችው ስጦታ የተለየ ነገር ላያስተውል ይችላል። ይሁን እንጂ የሌሎችን ልብ የማወቅ ችሎታ የነበረው ኢየሱስ “ድሃ መበለት” መሆኗን አውቋል። ምን ያህል ስጦታ እንዳስቀመጠችም በትክክል ያውቅ ነበር፤ “እጅግ አነስተኛ ዋጋ ያላቸው ሁለት ትናንሽ ሳንቲሞች” ነበሩ።b​—⁠ማርቆስ 12:​41, 42 NW

  • ይሖዋ በሙሉ ነፍስ የምታቀርቡትን አገልግሎት ከፍ አድርጎ ይመለከተዋል
    መጠበቂያ ግንብ—1997 | ጥቅምት 15
    • b እነዚህ ሳንቲሞች እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ሌፕተን ሲሆኑ በወቅቱ ይሠራባቸው ከነበሩት የአይሁዳውያን ሳንቲሞች ሁሉ የመጨረሻዎቹ ትንንሽ ሳንቲሞች ናቸው። የሁለት ሌፕታ ዋጋ የአንድ ቀን ምንዳ 1/64ኛ ነው። እንደ ማቴዎስ 10:​29 ገለጻ አንድ ሰው በአንድ አሳሪዮን ሳንቲም (ይህ ከስምንት ሌፕታ ጋር የሚተካከል ነው) ሁለት ድንቢጦች መግዛት ይችል ነበር፤ እነዚህ፣ ድሃ የሆኑ ሰዎች ለመብል የሚጠቀሙባቸው በጣም ርካሽ ወፎች ናቸው። ይህቺ መበለት ግን የነበራት ገንዘብ ለአንድ ጊዜ ምግብ እንኳ የማትበቃውን አንዲት ድንቢጥ ለመግዛት ከሚያስችለው ዋጋ ግማሽ ያህል ብቻ ነበር። በእርግጥም ይህች ሴት ድሃ ነበረች።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ